ልጁም ከመልአኩ ጋር ሄደ፥ ውሻውም ከኋላ ተከትሎአቸው ሄደ፥ ሲሄዱ ዋሉና ሲመሽ በጢግሮስ ወንዝ አጠገብ አረፉ።
ያም ልጅ ሊታጠብ ወረደ፤ ከውኃውም ውስጥ ዓሣ ወጥቶ ተወረወረ፤ ያንም ልጅ ይውጠው ዘንድ ወደደ።