መጽሐፈ ጦቢት 6:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጋኔኑ ጭሱ ሲሸተው ሽሽቶ ይሄዳል ወደ እርሷም ከቶ ተመልሶ አይመጣም። አብራችሁ ከመተኛታችሁ በፊት ሁለታችሁም ለመጸለይ ተነሱ፥ የሰማዩ ጌታ ጸጋውንና ከለላውን እንዲሰጣችሁ ለምኑት። አትፍራ! ከጥንት ጀምሮ እርሷ የተወሰነችው ለአንተ ነው፥ የምታድናትም አንተ ነህ። ቃሌን እሰጥሃለሁ እርሷ አንተን ትከተላለች፥ እንደ ወንድሞች የሚሆኑልህ ልጆችንም ትወልድልሃለች፥ አትጨነቅ።” ጦቢያ የሩፋኤልን ንግግር ባደመጠ ጊዜና እርሷ ከዘሩና ከአባቱ ወገን የሆነች እኀቱ መሆንዋን ባወቀ ጊዜ በጣም ወደዳት፥ ልቡም ከእርሷ ጋር ሆነ። |