ለቅጣት የተፈጠሩ ነፍሳት አሉ፤ በተቆጣም ጊዜ በመቅሰፍትነት ይልካቸዋል፤ በጥፋት ቀን ኃያልነታቸውን ያሳያሉ፤ የፈጣሪያቸውንም ቁጣ ያበርዳሉ።
ለበቀል የተፈጠረች መንፈስ አለች፤ በጥፋታቸው መቅሠፍታቸውን ያበዟታል፤ በዘመናቸው ኀይላቸው ይደክማል፤ የፈጣሪያቸው መቅሠፍትም ይመጣባቸዋል።