እነሆ፥ ኰብልዬ በራቅሁ በምድረ በዳም በተቀመጥሁ፥
ከዐውሎ ነፋስና ከውሽንፍር ሸሽቼ፣ ወደ መጠለያዬ ፈጥኜ በደረስሁ ነበር።”
ከዚህ ከደረሰብኝ ዐውሎ ነፋስና ሞገድ መጠለያ ስፍራ ለማግኘት ፈጥኜ በሄድኩ ነበር።
አምላኬ ሆይ፥ ሕይወቴን እነግርሃለሁ፤ እንባዬንም እንደ ትእዛዝህ በፊትህ አኖርሁ።
ምስጋና የሚገባውን ጌታን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።
ከቀኑ ሙቀት ጥላና መከለያ፤ ከውሽንፍርና ከዝናብም መጠጊያና መሸሸጊያ ስፍራ ይሆናል።