ከዚያም ዳዊት በኢየሩሳሌም ላሉት አገልጋዮቹ ሁሉ፥ “ተነሡ እንሽሽ፤ ያለበለዚያ ከአቤሴሎም እጅ ማምለጥ አንችልም፤ ፈጥኖ እንዳይዘን፥ ክፉም እንዳያመጣብን፤ ከተማዪቱንም በሰይፍ ስለት እንዳይመታ ፈጥናችሁ እንሂድ” አላቸው።
መዝሙር 55:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክንፍን ማን በሰጠኝ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ኰብልዬ በራቅሁ፣ በምድረ በዳም በሰነበትሁ ነበር፤ ሴላ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ሩቅ ስፍራ ተጒዤ መኖሪያዬን በበረሓ ባደረግሁ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምንም ምን አታድናቸውም፤ አሕዛብን በመዓትህ ትጥላቸዋለህ። |
ከዚያም ዳዊት በኢየሩሳሌም ላሉት አገልጋዮቹ ሁሉ፥ “ተነሡ እንሽሽ፤ ያለበለዚያ ከአቤሴሎም እጅ ማምለጥ አንችልም፤ ፈጥኖ እንዳይዘን፥ ክፉም እንዳያመጣብን፤ ከተማዪቱንም በሰይፍ ስለት እንዳይመታ ፈጥናችሁ እንሂድ” አላቸው።
ሁሉም አመንዝሮች፥ የአታላዮች ጉባኤ ናቸውና ሕዝቤን እንድተው፥ ከእነርሱም ተለይቼ እንድሄድ በምድረ በዳ የመንገደኞች ማደሪያን ማን በሰጠኝ?
ዳዊት በልቡ፦ “ከእነዚህ ቀናት በአንዱ በሳኦል እጅ መገደሌ ስለማይቀር፥ የሚበጀኝ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር መሸሽ ብቻ ነው፤ ከዚያ በኋላም ሳኦል በእስራኤል ሁሉ እኔን ማሳደዱን ይተዋል፤ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ” ብሎ አሰበ።