እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቆሮ አፉንም እንደማይከፍት ዲዳ ሆንሁ።
በርግጥም ጆሮው እንደማይሰማ፣ አንደበቱም መልስ መስጠት እንደማይችል ሰው ሆንሁ።
በእውነትም እንደማይሰማና መልስ ለመስጠት እንደማይችል ሰው ሆኜአለሁ።
ተጨነቀ፥ ተሰቀየም፥ አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና፥ በእንደዚህ ያለ ዘመን አስተዋይ የሆነ ሰው ዝም ይላል።
በጓደኛ አትታመኑ፥ በወዳጅም አትተማመኑ፤ የአፍህን ደጅ በጉያህ ከምትተኛው ጠብቅ።
የሚከሱበትን ምክንያት እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህንን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤