Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




አሞጽ 5:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና፥ በእንደዚህ ያለ ዘመን አስተዋይ የሆነ ሰው ዝም ይላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ አስተዋይ ሰው በእንዲህ ያለ ጊዜ ዝም ይላል፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህ ዘመኑ ክፉ ስለ ሆነ አስተዋይ የሆነ ሰው ዝም ይላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ስለ​ዚህ ዘመኑ ክፉ ነውና በዚያ ዘመን አስ​ተ​ዋይ ዝም ይላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




አሞጽ 5:13
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን በመጨረሻዎቹ ቀኖች የሚያስጨንቁ ጊዜያት እንደሚመጡ ይህን እወቅ።


ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በዚህ ቤተሰብ ላይ ክፉ አቅጃለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን ማውጣት አትችሉም፤ በትዕቢትም አትሄዱም፥ ጊዜው ክፉ ነውና።


ነገር ግን ሙግቴ ከካህን ጋር ነውና ማንም አይከራከር፥ ማንም አይዝለፍ።


ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፥ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፥


ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን የጦር ትጥቅ አንሡ።


እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።


የሞተውን ሰው የሚያቃጥለው ዘመዱ አጥንቱን ከቤቱ አንስቶት ባወጣው ጊዜ፥ በቤቱም በውስጠኛው ክፍል ያለውን፦ “በእዚያ እስከ አሁን ድረስ ከአንተ ጋር ሰው አለን?” ይለዋል፥ እርሱም፦ “ማንም የለም” ይላል፤ ያንጊዜ፦ “የጌታን ስም ልንጠራ አይገባንምና ዝም በል” ይለዋል።


እነርሱም፦ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል ለመውለድም ብርታቱ የለም።


እነርሱ ግን ዝም አሉ፥ ንጉሡ እንዳይመልሱለት አዝዞ ነበርና “አንዳችም አልመለሱለትም”።


ሰውም ጊዜውን አያውቅም፥ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።


ሕዝቡም ቀደም ሲል ንጉሥ ሕዝቅያስ ባዘዛቸው መሠረት አንዲት ቃል ሳይናገሩ ዝም አሉ፤


እነርሱ አልተናገሩምና፥ ቆመው ዳግመኛ አልመለሱምና እኔ በትዕግሥት እጠብቃለሁን?


እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቆሮ አፉንም እንደማይከፍት ዲዳ ሆንሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች