አቤቱ ጌታ፥ ዐይኖቼ ወደ አንተ ናቸውና፥ በአንተ ታመንሁ፥ ነፍሴን አትተዋት።
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ፤ መጠጊያዬም አንተ ነህ፤ እንግዲህ ነፍሴን አትተዋት።
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እኔ ግን በአንተ መተማመኔን አልተውም፤ የአንተንም ጥበቃ ስለምፈልግ እንድሞት አታድርገኝ!
አምላካችን ሆይ! አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን ልንቋቋመው አንችልም፤ ዐይኖቻችን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር የምናደርገውን ነገር አናውቅም።”
ጌታ ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና።
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር። በጌታ ታመንሁ፥ ነፍሴን፦ እንዴት እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ሽሺ ትሉአታላችሁ?
ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቁጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።
ድሆችና ምስኪኖችም ውኃ ይሻሉ አያገኙምም፥ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ ጌታ እሰማቸዋለሁ፥ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።
“ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።