በሞኝ አማካኝነት መልእክት የሚልክ፥ እግሮቹን ይቈርጣል፥ ግፍንም ይጠጣል።
በሞኝ እጅ መልእክትን መላክ፣ የገዛ እግርን እንደ መቍረጥ ወይም መርዝ እንደ መጋት ነው።
ሞኝን መልእክተኛ ማድረግ የገዛ እግርን እንደ መቊረጥና ዐመፅን እንደ መጋበዝ ይቈጠራል።
ሆምጣጤ ጥርስን፥ ጢስም ዓይንን እንደሚጐዳ፥ ሰነፍም ለላኩት እንዲሁ ነው።
መጥፎ መልእክተኛ በክፉ ላይ ይወድቃል፥ የታመነ መልእክተኛ ግን ፈውስ ነው።
ለላኩት የታመነ መልእክተኛ፥ በመከር ወራት ደስ እንዲሚያሰኝ የውርጭ ጠል ነው፥ የጌታውን ነፍስ ያሳርፋልና።
ለራሱ ጠቢብ የሆነ እንዳይመስለው ለሞኝ እንደ ሞኝነቱ መልስለት።
በምሳሌ የሚናገር ሞኝ፥ እንደተንጠለጠሉ የአንካሳ እግሮች ነው።
ከእርሱ ጋር ወጥተው የነበሩት ሰዎች ግን፦ “ከእኛ ይልቅ እነርሱ ብርቱ ናቸውና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም” አሉ።