ዘኍል 3:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀዓት ውስጥም የእንበረማውያን ወገን፥ የይስዓራውያንም ወገን፥ የኬብሮናውያንም ወገን፥ የዑዝኤላውያንም ወገን ይካተቱ ነበር፤ የቀዓታውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእንበረማውያን፣ የይስዓራውያን፣ የኬብሮናውያንና የዑዝኤላውያን ጐሣዎች ከቀዓት ወገን ናቸው፤ እነዚህ የቀዓት ጐሣዎች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዓምራም፥ የይጽሃር፥ የኬብሮንና የዑዚኤል ቤተሰቦች በቀዓት ጐሣ ውስጥ ተጠቃለው ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቀዓትም የእንበረም ወገን፥ የይስዓር ወገን፥ የኬብሮንም ወገን፥ የአዛሔልም ወገን ነበሩ፤ የቀዓት ወገኖች እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቀዓትም የእንበረማውያን ወገን፥ የይስዓራውያንም ወገን፥ የኬብሮናውያንም ወገን፥ የዑዝኤላውያንም ወገን ነበሩ፤ የቀዓታውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው። |
ከኬብሮናውያን ሐሸብያና ወንድሞቹ፥ ጽኑዓን የነበሩት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ለጌታ ሥራ ሁሉ ለንጉሡም አገልግሎት በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ባለው በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር።
ወንዶች ሁሉ እንደ ቁጥራቸው ዕድሜው አንድ ወር የሞላውና ከዚያም በላይ ያለው ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ፤ የመቅደሱንም ግዴታ ለመፈጸም የተዘጋጁ ነበሩ።