ዘኍል 26:59 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። እርሷ በግብጽ ከሌዊ የተወለደች የሌዊ ልጅ ነበረች፤ ለእንበረምም አሮንንና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእንበረም ሚስቱ ዮካብድ ትባል ነበር፤ እርሷም በግብጽ አገር ከሌዋውያን የተወለደች የሌዊ ዘር ነበረች። ከእንበረምም አሮንን፣ ሙሴንና እኅታቸውን ማርያምን ወለደች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓሞራም በግብጽ የተወለደችውን የሌዊን ሴት ልጅ ዮኬቤድን አግብቶ ነበር፤ እርስዋም አሮንና ሙሴ የተባሉትን ሁለት ወንዶች ልጆችንና ማርያም የተባለችውን አንዲት ሴት ልጅ ወለደችለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቆሬ ወገን፥ የቀዓት ወገን። ቀዓትም እንበረምን ወለደ። በግብፅ ሀገር እነዚህን ሌዋውያንን የወለደቻቸው የሌዊ ልጅ የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። ለእንበረምም አሮንንና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። እርስዋ በግብፅ ከሌዊ የተወለደች የሌዊ ልጅ ነበረች፤ ለእንበረምም አሮንንና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት። |
የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ፤ ማርያምም በዚያ ሞተች፥ በዚያም ተቀበረች።