ዘኍል 11:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ለአባቶቻቸው ወደ ማልህላቸው ምድር እንዳደርሳቸው፦ ‘ሞግዚት የሚጠባውን ልጅ እንደምታቅፈው እንዲሁ በብብትህ እቀፋቸው’ የምትለኝ፥ በውኑ ይህን ሕዝብ ሁሉ እኔ ፀነስሁትን? እነርሱንስ ወልጃቸዋለሁን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ሁሉ ሕዝብ የፀነስሁት እኔ ነኝን? እኔስ ወለድሁትን? ታዲያ ሞግዚት ሕፃን እንደምትታቀፍ በክንዴ ታቅፌ ለቀድሞ አባቶቻቸው ትሰጣቸው ዘንድ በመሐላ ቃል ወደ ገባህላቸው ምድር እንዳስገባቸው የምትነግረኝ ለምንድን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጡት የሚጠባውን ሕፃን አንዲት ሞግዚት እንደምትታቀፈው እኔም እነርሱን ታቅፌ አንተ ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባህላቸው ምድር እንዳደርሳቸው የምታደርገኝ እነዚህን ሰዎች እኔ ፀነስኳቸውን? ወይስ እኔ ወለድኳቸውን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ለአባቶቻቸው ወደ ማልህላቸው ምድር አደርሳቸው ዘንድ፦ ሞግዚት የሚጠባውን ልጅ እንድታቅፍ በብትህ እቀፋቸው የምትለኝ፥ በውኑ ይህን ሕዝብ ሁሉ እኔ ፀነስሁትን? ወይስ ወለድሁትን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ለአባቶቻቸው ወደ ማልህላቸው ምድር አደርሳቸው ዘንድ፦ ሞግዚት የሚጠባውን ልጅ እንድታቅፍ በብብትህ እቀፋቸው የምትለኝ፥ በውኑ ይህን ሕዝብ ሁሉ እኔ ፀነስሁትን? ወለድሁትንስ? |
ከአባቴ ቤት ከተወለድሁባት ምድርም ያወጣኝ፦ ‘ይህችንም ምድር ለዘርህ እሰጥሃለሁ’ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል፥ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ።
በዚህች ምድር ተቀመጥ፥ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፥ እባርክሃለሁም፥ እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህ ለአብርሃም የማልሁለትንም መሐላ አጸናለሁ።
ዮሴፍም ወንድሞቹን፦ “እኔ እሞታለሁ፥ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፥ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል” አላቸው።
ብዛታቸው ሰባ የሚሆን የአክዓብ ልጆች በሰማርያ ከተማ ይኖሩ ነበር፤ ኢዩ ደብዳቤ ጽፎ የደብዳቤውን አንዳንድ ቅጂ ለከተማይቱ ገዢዎች፥ ለታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና የአክዓብን ተወላጆች ለሚያሳድጉ ሞግዚቶች ሁሉ ላከ፤ የደብዳቤውም ቃል፥
ስለዚህም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊና የከተማይቱ ገዢ ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና ከአሳዳጊ ሞግዚቶች ጋር በመተባበር ለኢዩ “እኛ አገልጋዮችህ ነን፤ አንተ የምታዘንን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ነን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ አንተ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” ሲሉ መልእክት ላኩ።
ጌታም ወደ ከነዓናውያን፥ ወደ ኬጢያውያን፥ ወደ አሞራውያን፥ ወደ ኤዊያውያን፥ ወደ ኢያቡሳውያንም ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር ባገባህ ጊዜ ይህችን አገልግሎት በዚህ ወር ታገለግላለህ።
ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ሂድ፥ አንተ ከግብጽ ምድር ካወጣኸው ሕዝብ ጋር ከዚህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ‘ለዘርህ እሰጣታለሁ’ ብዬ ወደ ማልሁባት ምድር ውጣ፤
ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ እሰጣታለሁ ብዬ እጄን ወደ አነሳሁባት ምድር አመጣችኋለሁ፤ እርሷንም ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ ጌታ ነኝ።’”
በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ የተወለደው ሕጻን ልጇን ትረሳለች? ርህራሄ አልባስ እስክመሆን ትደርሳለች? አዎን፥ እርሷ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም።
ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፥ እቴጌዎቻቸውም ሞግዝቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፥ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።
ወደዚህም ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ፥ በምድረ በዳም፥ ሰው ልጁን እንደሚንከባከብ፥ ጌታ አምላካችሁ እንዴት እንደተንከባከባችሁ አይታችኋል።’
ዳሩ ግን የክርስቶስ ሐዋርያት እንደ መሆናችን መጠን ልንጫናችሁ በቻልን ነበር፤ ነገር ግን ሞግዚት የራስዋን ልጆች እንደምትንከባከብ፥ በመካከላችሁ የዋሆች ሆንን፤