ዘኍል 10:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሮቤልም ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር አለቃ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም የሮቤል ሰፈር ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ሆነው ተጓዙ፤ አለቃቸውም የስዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም በሮቤል ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙት በሸዴኡር ልጅ በኤሊጹር መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሮቤልም ሰፈር በሥርዐታቸው ከየሠራዊቶቻቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር አለቃ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሮቤልም ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር አለቃ ነበረ። |
ሁለተኛውንም የማስጠንቀቂያ መለከት ከፍ ባለ ድምፅ ስትነፉ በደቡብ በኩል የሰፈሩት ይጓዛሉ፤ የማስጠንቀቅያውን መለከት እንዲጓዙ ለመቀስቀስ ይነፋሉ።
ለአንድነትም መሥዋዕት ሁለት በሬዎች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ የሰዲዮር ልጅ የኤሊሱር መባ ይህ ነበረ።