ነህምያ 2:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡን እንዲህ አልኩት፦ “ንጉሡ መልካም ፈቃዱ ቢሆን፥ ይሁዳ እስክደርስ ድረስ እንዲያሳልፉኝ ከወንዙ ማዶ ላሉት ገዢዎች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እንዲህ አልሁት፤ “ንጉሡን ደስ የሚያሠኘው ቢሆን፣ ይሁዳ እስክደርስ ድረስ በደኅና እንዲያሳልፉኝ ከኤፍራጥስ ማዶ ላሉት አገረ ገዦች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በመቀጠል ወደ ይሁዳ ማለፍ እንዲፈቅዱልኝ ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ በሚገኘው ክፍለ ሀገር ላሉት አገረ ገዢዎች የይለፍ ደብዳቤ እንዲሰጠኝ ለንጉሠ ነገሥቱ ልመና አቀረብኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡንም፥ “ንጉሥ ደስ ቢለው፥ እስከ ይሁዳ ሀገር እንዲያደርሱኝ በወንዝ ማዶ ላሉት ገዦች ደብዳቤ ይስጠኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡንም፦ “ንጉሡ ደስ ቢለው፥ እስከ ይሁዳ አገር እንዲያደርሱኝ በወንዝ ማዶ ላሉት አገረ-ገዦች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤ |
እኔም ንጉሡ አርጤክስስ በወንዝ ማዶ ለምትገኙ ገንዘብ ያዦች ሁሉ፦ የሰማያት አምላክ ሕግ ጸሐፊ የሆነው ካህኑ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ሁሉ በትጋት እንድትሰጡት ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፤
ንጉሡንም፦ “የአምላካችን እጅ በሚፈልጉት ሁሉ ላይ ለመልካም ነው፥ ኃይሉና ቁጣውም እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተናግረን ነበርና በመንገድ ካለው ጠላት እንዲያድኑን ወታደሮችና ፈረሰኞች ከንጉሡ ለመጠየቅ አፍሬ ነበር።