ነህምያ 10:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማዓዝያ፥ ቢልጋይ፥ ሽማዕያ፤ እነዚህ ካህናት ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌዋውያኑ፦ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፣ ከኤንሐዳድ ወንዶች ልጆች ቢንዊ፣ ቀድምኤል፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሌዋውያን ወገን፦ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥ የሔናዳድ ጐሣ የሆነው ቢኑይ፥ ቃድሚኤል፥ ሸባንያ፥ ሆዲያ፥ ቀሊጣ፥ ፐላያ፥ ሐናን፥ ሚካ፥ ረሖብ፥ ሐሻብያ፥ ዛኩር፥ ሼሬብያ፥ ሸባንያ፥ ሆዲያ፥ ባኒና በኒኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋውያኑም የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥ ከኢንሐዳድ ልጆች ባንዩ፥ ቀዳምኤል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌዋውያኑም፥ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥ ከኤንሐዳድ ልጆች ቢንዊ፥ |
የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሻብያ፥ ሼሬብያ፥ የቃድሚኤል ልጅ ኢያሱና ወንድሞቻቸው ደግሞ ከፊት ለፊታቸው ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ክፍል በክፍል ትይዩ ሆነው ያወድሱና ያመሰግኑ ነበር።
ደግሞ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ሼሬብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሻብታይ፥ ሆዲያ፥ ማዓሤያ፥ ቅሊጣ፥ አዛርያ፥ ዮዛባድ፥ ሐናን፥ ፐላያና ሌዋውያኑ ሕጉን ለሕዝቡ ያስረዱ ነበር፤ ሕዝቡም በቆሙበት ነበሩ።