ኤርምያስ 51:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከለዳውያንም ምድር ተገድለው፥ በሜዳዋም ላይ ተወግተው ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባቢሎን ምድር ታርደው፣ በአደባባዮቿም እስከ ሞት ቈስለው ይወድቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወታደሮችዋ በከተሞቻቸው መንገዶች ላይ ቈስለው ይሞታሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተገደሉት በከለዳውያን ምድር ይወድቃሉ፤ የቈሰሉትም በውጭ ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከለዳውያንም ምድር ተገድለው፥ በሜዳዋም ላይ ተወግተው ይወድቃሉ። |
አንተ ግን እንደ ተጠላ ቅርንጫፍ ከመቃብርህ ተጥለሃል፤ በሰይፍም የተወጉት፥ ተገድለውም ወደ ጉድጓዱ ድንጋዮች የወረዱ ከድነውሃል፤ እንደተረገጠም ሬሳ ሆነሃል።
ሰይፍ በፈረሶችዋና በሰረገሎችዋ ላይ በመካከልዋም ባሉት በባዕድ ሕዝብ ሁሉ ላይ አለ፥ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍም በመዝገቦችዋ ላይ አለ እነርሱም ይበዘበዛሉ።