ያዕቆብ 1:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፀሐይ ቃጠሎ በንዳዱ ሲወጣ ሣሩን ያደርቀዋል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የመልኩም ውበት ይጠፋል፤ እንዲሁ ሀብታም ሰው በመንገዱ ይዝላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፀሓይ በነዲድ ሙቀቷ ወጥታ ሣሩን ታጠወልጋለችና፤ አበባው ይረግፋል፤ ውበቱም ይጠፋል፤ እንዲሁም ባለጠጋ ሰው፣ በዕለት ተግባሩ ሲዋትት ሳለ ይጠፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፀሐይ ከሙቀቱ ጋር ሲወጣ ሣሩን ያደርቀዋል አበባውም ይረግፋል፤ ውበቱም ይጠፋል፤ እንዲሁም ሀብታም ሰው በሥራው ሲባክን ይጠፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል። |
ለኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል ለሆነች፥ በወይን ጠጅ ለተሸነፉ፥ በለምለሙ ሸለቆአቸው ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብሩ ጌጥ አበባ ወዮላት!
በለምለሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች የረገፈች የክብሩ ጌጥ አበባ ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች፤ያያት ሁሉ እጁን ሰዶ ይበላታል።
ነገር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እግዚአብሔር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም?