ርብቃም ይስሐቅን አለችው፦ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፥ ያዕቆብ ከዚህ አገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለምኔ ነው?”
ዘፍጥረት 36:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፥ የኬጢያዊውን የዔሎንን ልጅ ዓዳን፥ የሒዋዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳትን ኦሆሊባማን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሳው ከከነዓን ሴቶች አገባ፤ እነርሱም፦ የኬጢያዊው የኤሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤዊያዊው የፂብዖን ልጅ ዓና የወለዳት ኦሆሊባማ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሳው ከነዓናውያን ሴቶችን አገባ፤ እነርሱም የሒታዊው የኤሎን ልጅ ዓዳ፥ የሒዋዊው የጺባዖን ልጅ ዐና የወለዳት ኦሆሊባማን እና፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ የኬጤያዊውን የዔሎን ልጅ ሐዳሶን፥ የኤውያዊው የሴቤሶ ልጅ ሐና የወለዳትን ኤሌባማን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ የኬጢያዊውን የዔሎንን ልጅ ዓዳን የኤዊያዊው የፅብዖን ልጅ ዓን የወለዳትን አህሊባማም፥ |
ርብቃም ይስሐቅን አለችው፦ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፥ ያዕቆብ ከዚህ አገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለምኔ ነው?”
ዔሳው ወደ እስማኤል ሄደ፥ ማዕሌትንም በፊት ካሉት ሚስቶቹ ጋር ሚስት ትሆነው ዘንድ አገባ፥ እርሷም የአብርሃም ልጅ የሆነ የእስማኤል ልጅና የነባዮት እኅት ናት።