Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 27:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 ርብቃም ይስሐቅን አለችው፦ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፥ ያዕቆብ ከዚህ አገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለምኔ ነው?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ከዚያም ርብቃ ይሥሐቅን፣ “ዔሳው ባገባቸው በኬጢያውያን ሴቶች ምክንያት መኖር አስጠልቶኛል፤ ያዕቆብም ከዚሁ አገር ከኬጢያውያን ሴቶች ሚስት የሚያገባ ከሆነ፣ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 ርብቃ ይስሐቅን “ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሒታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱን ካገባ ከመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 ርብ​ቃም ይስ​ሐ​ቅን አለ​ችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተ​ነሣ ሕይ​ወ​ቴን ጠላ​ሁት፤ ያዕ​ቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን የሚ​ያ​ገባ ከሆነ በሕ​ይ​ወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 ርብቃም ይስሐቅን አለችው፦ ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት ያዕቆብ ከዚህ አገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለምኔ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 27:46
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፥ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፥


የከነዓናውያንም ሴቶች ልጆች በአባቱ በይስሐቅ ፊት የተጠሉ እንደ ሆኑ ዔሳው ባየ ጊዜ፥


ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጉዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “ጌታ ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።


በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ! ቁጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ!


ሕይወቴን ናቅኋት፥ ለዘለዓለም ልኖር አልወድድም፥ ቀኖቼ እስትንፋስ ናቸውና ተወኝ።


አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ከሕይወት ሞት ይሻላልና፥ እባክህ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ።”


እግዚአብሔርም ዮናስን “ስለዚች የጉሎ ተክል ልትቆጣ ይገባህልን?” አለው። እርሱም፦ “እስከ ሞት ድረስ ልቆጣ ይገባኛል” አለ።


እንዲህስ ከምታደርግብኝ፥ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ፥ በእኔ ላይ የሚሆነውን መከራ እንዳላይ፥ እባክህ፥ ፈጽሞ ግደለኝ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች