የላጣቸውንም በትሮች በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ በበጎች ፊት አኖራቸው፥ በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ ይጎመጁ ነበር።
ዘፍጥረት 30:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፥ የበረቱት በጎች በጎመጁ ጊዜ፥ በጎቹ በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ ከበጎቹ ፊት አደረገ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ብርቱ እንስቶች አውራ ፈልገው በሚቅበጠበጡበት ጊዜ፣ በትሮቹ አቅራቢያ እንዲጠቁ በትሮቹን በውሃ ገንዳዎቹ ውስጥ ፊት ለፊታቸው ያስቀምጥ ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጤናማና ብርቱ የሆኑት መንጋዎች ፍትወት እየተሰማቸው ሲጐመዡ ያዕቆብ በትሮቹን በፊታቸው ባሉት ውሃ መጠጫዎች ውስጥ ያኖራቸው ነበር፤ በዚህ ዐይነት በትሮቹን እያዩ ይፀንሱ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፦ በጎቹ በሚፀንሱበት ወራት በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በበጎቹ ፊት በውኃ ማጠጫ ገንዳው ውስጥ ያኖራቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፤ የበረቱት በጎች በጎመጁ ጊዜ፥ በጎቹ በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ ከበጎቹ ፊት አደረገ፤ |
የላጣቸውንም በትሮች በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ በበጎች ፊት አኖራቸው፥ በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ ይጎመጁ ነበር።
ያዕቆብም ጠቦቶቹን ለየ፥ ሽመልመሌ መሳይና ጥቁር ያለባቸውን በጎቹንም ሁሉ በላባ በጎች ፊት ለፊት አኖረ፥ መንጎቹንም ለብቻቸው አቆማቸው፥ ወደ ላባም በጎች አልጨመራቸውም።