ይህን መናገሩንም ሳይፈጽም እነሆ፥ ሚልካ የወለደችው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በጫንቃዋ ተሸክማ ወጣች፥ ሚልካም የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት ናት።
ዘፍጥረት 29:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ የላባ ልጅ ራሔል ከአባትዋ በጎች ጋር ደረሰች፥ እርሷ የአባትዋን በጎች ትጠብቅ ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ከእረኞቹ ጋራ በመነጋገር ላይ ሳለ፣ ራሔል፣ እረኛ ነበረችና የአባቷን በጎች እየነዳች መጣች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም ከእረኞቹ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ወደዚያ መጣች፤ እርስዋ የበጎች እረኛ ነበረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ፥ የላባ ልጅ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ደረሰች፤ እርስዋ የአባቷን በጎች ትጠብቅ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ የላባ ልጅ ራሔል ከአባትዋ በጎች ጋር ደረስች እርስዋ የአባትዋን በጎች ትጠብቅ ነበርና። |
ይህን መናገሩንም ሳይፈጽም እነሆ፥ ሚልካ የወለደችው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በጫንቃዋ ተሸክማ ወጣች፥ ሚልካም የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት ናት።
ያዕቆብም የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የአጎቱን የላባን በጎች ባየ ጊዜ፥ ቀረበ ከጉድጓዱም አፍ ድንጋዩን ገለበጠ፥ የአጎቱን የላባን በጎችንም አጠጣ።
በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፥ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፥ “ባለ ራእዩ እዚህ አለን?” ሲሉ ጠየቋቸው።