ዘዳግም 27:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “‘ዐይነ ስውሩን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ፥ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዐይነ ስውሩን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ፣ የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘ዕውርን ወደተሳሳተ አቅጣጫ የሚመራ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዕውሩን ከመንገድ ፈቀቅ የሚያደርግ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕውሩን ከመንገድ ፈቀቅ የሚያደርግ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። |
ጉበኞቹ ዕውሮች ናቸው፥ ሁሉም እውቀት የላቸውም፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም፤ ሕልምን ያልማሉ፤ ይተኛሉ፤ እንቅልፍ ይወድዳሉ።
ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ፤ ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበለዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር አሉና።