ዘዳግም 26:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፥ ስትወርሳትና ስትኖርባት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፣ ስትወርሳትና ስትኖርባት፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህ እንድትወርሳት ወደሚሰጥህ ምድር ገብተህ በምትወርሳትና ተደላድለህ በምትቀመጥባት ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ፥ በወረስሃትም፥ በኖርህባትም ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር በገባህም ጊዜ፥ በወረስሃትም በኖርህባትም ጊዜ፥ |
“አምላክህ ጌታ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፥ በምትወርሳትና በምትቀመጥባት ምድር፥ ‘በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ፥ እኔም በላዬ ንጉሥ ላንግሥ’ ብትል፥
ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ ባሳረፈህ ጊዜ፥ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ መደምሰስን፥ ይህንን አትርሳ።”
ጌታ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ሰብል በኲራቱን ሁሉ ውሰድ፤ በቅርጫትም ውስጥ አድርገው፤ ከዚያም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ጌታ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ።
በእናንተ ቃላት ምክንያት ጌታ እኔን ተቆጣኝ፤ ዮርዳኖስንም እንዳልሻገር ጌታ አምላካችሁ ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደ መልካሚቱ ምድር እንዳልገባ ማለ።
አንተ ግን እዚህ እኔ አጠገብ ቁም፤ እኔ በምሰጣቸው ምድር እነዚህን በመጠበቅ እንዲኖሩ፥ ሕግጋቴን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቶቼን ሁሉ እነግርሃለሁ።’
“ጌታ አምላክህ ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከአንተ የበለጡትን እና የበረቱትን ሰባቱን አሕዛብ፥ ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ አሞራውያን፥ ከነዓናውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ ከፊትህም ብዙ አሕዛብን ባስወጣልህ ጊዜ፥