ዘዳግም 22:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንድምህ አህያ ወይም በሬው በመንገድ ወድቆ ብታይ ከእርሱ ጋር ሆነህ በማንሣት እርዳው እንጂ ቸል አትበለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወንድምህ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታየው፣ በእግሩ እንዲቆምለት ርዳው እንጂ ዐልፈኸው አትሂድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤላዊ ወገንህ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታይ ዝም ብለህ አትለፍ፤ ቆሞ እንዲሄድ እንስሳውን በማንሣት እርዳው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወንድምህ አህያው ወይም በሬው በመንገድ ወድቆ ብታይ ቸል አትበላቸው፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር ሆነህ አነሣሣው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድምህ አህያ ወይም በሬው በመንገድ ወድቆ ብታይ ከእርሱ ጋር ሆነህ አነሣሣው እንጂ ቸል አትበለው። |
እንደዚሁም ሁሉ በአህያው ወይም በልብሱ ታደርጋለህ፥ ወንድምህ በጠፋው ማንኛውም ነገር ሁሉ ባገኘኸው ጊዜ ታደርጋለህ፥ ቸል ልትለውም አይገባህም።