ዘዳግም 15:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገር ግን አምላክህ ጌታ ትወርሳት ዘንድ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ውስጥ አብዝቶ ስለሚባርክህ፥ በመካከልህ ድኻ አይኖርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ውስጥ አብዝቶ ስለሚባርክህ፣ በመካከልህ ድኻ አይኖርም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ ዛሬ በማዝህ ትእዛዞች ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ታዛዥ ሆነህ ብትገኝ፥ እግዚአብሔር አብዝቶ ስለሚባርክህ እርሱ በርስትነት በሚሰጥህ ምድር በመካከልህ ድኻ አይኖርም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ አምላክህ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይባርክሃልና በመካከልህ ድሃ አይኖርም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ ርስት አድርጎ በሰጠህ ምድር ላይ እግዚአብሔር በእውነት ይባርክሃልና አንተም የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽመህ ብትሰማ፥ ታደርጋትም ዘንድ ዛሬ የማዝዝህን ይህችን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቅ፥ በመካከልህ ድሃ አይኖርም። |
ይህን የምታደርገው የራሱ ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ሌዋዊና መጻተኛ፥ በከተሞችህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች መጥተው እንዲበሉና እንዲጠግቡ፥ አንተንም አምላክህ ጌታ በእጆችህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነው።
በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ “ጌታ አምላካችሁ ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ የእናንተ ጦር ሰዎች ሁሉ ታጥቀው በወንድሞቻችሁ በእስራኤል ልጆች ፊት ትሻገራላችሁ።
በእናንተ ቃላት ምክንያት ጌታ እኔን ተቆጣኝ፤ ዮርዳኖስንም እንዳልሻገር ጌታ አምላካችሁ ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደ መልካሚቱ ምድር እንዳልገባ ማለ።