2 ሳሙኤል 19:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በገዛ ከተማዬ ሞቼ በአባቴና በእናቴ መቃብር አጠገብ እንድቀበር፥ እባክህ፥ አገልጋይህን አሰናብተውና ይመለስ፤ ነገር ግን አገልጋይህ ኪምሃም እነሆ፤ ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር ይሻገር፤ ደስ ያለህንም ነገር አድርግለት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም፣ “ከመዓም ከእኔ ጋራ ይሻገራል፤ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም ሁሉ አደርግለታለሁ፤ ከእኔ የምትፈልገውን ማንኛውንም ነገር ለአንተም አደርግልሃለሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “እርሱን ይዤ እሄዳለሁ፤ እንዳደርግለት የምትፈልገውንም ሁሉ አደርግለታለሁ፤ ለአንተም ቢሆን የምትጠይቀውን ሁሉ እፈጽማለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “ከመዓም ከእኔ ጋር ይሻገር፤ በፊቴ ደስ የሚያሰኘኝንም አደርግለታለሁ፤ አንተም ከእኔ የምትሻውን ነገር ሁሉ አደርግልሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም፦ ከመዓም ከእኔ ጋር ይለፍ፥ ደስ የሚያሰኝህንም አደርግለታለሁ፥ አንተም ከእኔ የምትሻውን ሁሉ አደርግልሃለሁ አለው። |
ንጉሡም፥ “ኪምሃም ከእኔ ጋር ይሻገራል፤ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም ሁሉ አደርግለታለሁ፤ ከእኔ የምትፈልገውን ማናቸውንም ነገር ለአንተም አደርግልሃለሁ” አለው።
“ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ የቸርነት ሥራ ስላደረጉልኝ ለገለዓዳዊው ለባርዚላይ ልጆች ግን መልካም ነገር በማድረግ ተንከባከባቸው፤ በማዕድህም ከሚመገቡት መካከል ይሁኑ።