ወዲያውኑም በባሕር አጠገብ የሚገኙትን ከተሞች አይሁዳውያን ባሮችን ለመግዛት እንዲመጡ ጥሪ አደረገላቸው፤ በአንድ መክሊት ዘጠኝ ሰዎች እንደሚሸጥላቸው ተስፋ ሰጣቸው፤ ሁሉን ከሚችል አምላክ የሚመጣበትን በቀል አላሰበም ነበር።