ነገር ግን ሊስያስ ነገሩን ልብ አድርጐ ተመለከተና የደረሰበትን መሸነፍ አሰበ፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ረዳታቸው በመሆኑ ዕብራውያን የማይሸነፉ መሆናቸው ስለገባው መልእተኞች ወደ እነርሱ ላከ፤