1 ሳሙኤል 14:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳኦል ሚስት አሒኖዓም የምትባል የአሒማዓጽ ልጅ ነበረች፤ የሠራዊቱም አዛዥ አበኔር የሚባል የሳኦል አጎት የኔር ልጅ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳኦል ሚስት አኪናሆም የምትባል የአኪማአስ ልጅ ነበረች፤ የሰራዊቱም አዛዥ አበኔር የሚባል የአጎቱ የኔር ልጅ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስቱም አሒኖዓም ተብላ የምትጠራ የአሒማዓጽ ልጅ ነበረች፤ የሠራዊቱም አዛዥ አበኔር ተብሎ የሚጠራው የአጐቱ የኔር ልጅ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልም ሚስት ስም የአኪማኦስ ልጅ አኪናሆም ነበረች፤ የሠራዊቱም አለቃ ስም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አቤኔር ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም ሚስት ስም የአኪማአስ ልጅ አኪናሆም ነበረ፥ የሠራዊቱም አለቃ ስም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አበኔር ነበረ። |
አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።
ባለ ራእዩም ሳሙኤል፥ የቂስም ልጅ ሳኦል፥ የኔርም ልጅ አበኔር፥ የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ የቀደሱት ንዋየ ቅድሳት ሁሉ ከሰሎሚትና ከወንድሞቹ ሥልጣን በታች ነበረ።
በዚህ ጊዜ የሳኦል አጎት እርሱንና አገልጋዩን፥ “የት ነበራችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እርሱም፥ “አህዮቹን ፍለጋ ሄደን ነበር፤ እንደማይገኙ በተረዳን ጊዜ ግን ወደ ሳሙኤል ሄድን” አለው።
ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመግጠም ሲሄድ ሳኦል ተመልክቶ የሠራዊቱን አዛዥ አበኔርን፥ “አበኔር ሆይ፤ ይህ ልጅ የማን ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ አላውቅም” ብሎ መለሰለት።
ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ፥ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ። ሠራዊቱ በዙሪያው ሰፍሮ፥ ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ነበር።