1 ሳሙኤል 14:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ለሳኦል፥ “እነሆ፤ ሕዝቡ ሥጋውን ከነደሙ በመብላት ጌታን እየበደለ ነው” ተብሎ ተነገረው። ሳኦልም፥ “ይህ የክሕደት ተግባር ነው! አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ ወደዚህ አምጡልኝ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ለሳኦል፣ “እነሆ፤ ሕዝቡ ሥጋውን ከነደሙ በመብላት እግዚአብሔርን እየበደለ ነው” ተብሎ ተነገረው። ሳኦልም፣ “ሕግ ተላልፋችኋል፤ በሉ አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ አቅርቡልኝ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሳኦልም “ተመልከት ሕዝቡ ደም ያለበትን ሥጋ በመብላታቸው በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት ሠርተዋል” የሚል ወሬ ደረሰው። ሳኦልም “ይህ የክሕደት ተግባር ነው! አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ ወደዚህ አምጡልኝ” ሲል ጮኸባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሳኦልም፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ ከደሙ ጋር በመብላታቸው እግዚአብሔርን በደሉ” ብለው ነገሩት። ሳኦልም በጌቴም “ትልቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ አቅርቡልኝ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሳኦልም፦ እነሆ፥ ሕዝቡ ከደሙ ጋር በመብላታቸው እግዚአብሔርን በደሉ ብለው ነገሩት። ሳኦልም፦ እጅግ ተላለፋችሁ፥ አሁንም ትልቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ አቅርቡልኝ አላቸው። |
“ከእስራኤልም ልጆች ወይም በመካከላቸው ከሚኖር እንግዳ ማናቸውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊርበታለሁ፥ ያንንም ሰው ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።
ስለዚህ አንተ የምትፈርድ ሰው ሆይ! የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ ፈራጅ የሆንከው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና።
ሳኦልም፥ “በሕዝቡ መካከል እየዞራችሁ፥ ‘እያንዳንዳችሁ በሬዎቻችሁንና በጎቻችሁን አምጡ፤ እዚሁ ዐርዳችሁ ብሉ፤ ነገር ግን ሥጋውን ከነደሙ በመብላት ጌታን አትበድሉ’ በሏቸው” አለ። ስለዚህ በዚያች ሌሊት እያንዳንዱ ሰው በሬውን አምጥቶ በዚያ አረደው።