1 ሳሙኤል 13:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ አንድ የፍልስጥኤማውያን የጦር ምድብ የሚክማስን መተላለፊያ ለመቆጣጠር ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ አንድ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ወደ ማክማስ መተላለፊያ ወጥቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን የሚክማስን መተላለፊያ የሚቈጣጠር አንድ ቡድን ላኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ጥቂቶች ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወደ ማኪማስ መተላለፊያ ወጡ። |
ፍልስጥኤማውያን ሠላሳ ሺህ ሠረገሎች፥ ስድስት ሺህ ፈረሰኞች ቁጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤትአዌን በስተ ምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ።
አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና በሌላ በኩል ወዳለው የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር እንሻገር” አለው። ይህን ግን ለአባቱ አልነገረውም ነበር።