የሮማውያን ዝና ወደ ይሁዳ ጆሮ ደረሰ፤ እነርሱ ጐበዝ ጦረኞች ነበሩ፤ ከጐናቸው ለማሰለፉ ሰዎች ሁሉ ደጐች ነበሩ፤ ወደ እነርሱ ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ ወዳጅነታቸውን የሚሰጡ (የሚለግሡ) ነበሩ፤ ጀግና ጦረኞች ነበሩ።