ይሁዳ ከወንድሞቹ ጋር ሆኖ በደቡብ አውራጃ ከዔሳው ልጆች (ኤዱማውያን) ጋር ለመዋጋት ሄደ፤ ሔብሮንና መንደሮችዋን ያዘ፤ ምሽጐቿን አፈረሰ፥ የመካበቢያውን ረጃጅም ግንቦች በእሳት አጋየ።