1 ቆሮንቶስ 7:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፤ እንደዚሁም ደግሞ ሚስት ለባሏ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባል ለሚስቱ የሚገባትን ሁሉ ያድርግላት፤ ሚስትም ለባሏ እንዲሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባል ለሚስቱ ማድረግ የሚገባውን የጋብቻ መብትዋን አይከልክላት፤ እንዲሁም ሚስት ለባልዋ ማድረግ የሚገባትን የጋብቻ መብቱን አትከልክለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሚስትም ባልዋ የሚገባትን ያድርግላት፤ እንዲሁ ሚስትም ለባልዋ የሚገባውን ታድርግለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፥ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ። |
ሚስት በገዛ ሰውነቷ ላይ ሥልጣን የላትም፤ ሥልጣን ለባሏ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሰውነቱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ።
እናንተም ባሎች ሆይ! ጸሎታችሁ እንዳይደናቀፍ ከሚስቶቻችሁ ጋር በመተሳሰብ ኑሩ፤ የሕይወትንም ጸጋ አብረዋችሁ ስለሚወርሱ እንደ ደካማነታቸው ሴቶችን አክብሯቸው።