Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሶፎንያስ 3:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከጉባኤው ርቀው የሚያዝኑትን፥ ከአንቺም የሆኑትን እሰበስባለሁ፣ ስድብ እንደ ሸክም ከብዶባቸው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “ስለ ክብረ በዓላት መተጓጐል የተከዝሽበትን፣ የስድብሽን ሸክም፤ ከአንቺ አስወግዳለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከበዓሉ ርቀው የሚያዝኑትን፥ ከአንቺም የሆኑትን እሰበስባለሁ፤ ስድብ እንደ ሸክም ከብዶባቸው ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በበዓል ቀን እንደሚደረገው የደስታ ስሜት እንዲሰማሽ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ምንም ኀፍረት አይደርስብሽም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከጉባኤው ርቀው የሚያዝኑትን፥ ከአንቺም የሆኑትን እሰበስባለሁ፥ ስድብ እንደ ሸክም ከብዶባቸው ነበር።

参见章节 复制




ሶፎንያስ 3:18
18 交叉引用  

በጦ​ራ​ቸው ምድ​ርን አል​ወ​ረ​ሱም፥ ክን​ዳ​ቸ​ውም አላ​ዳ​ና​ቸ​ውም፤ ቀኝ​ህና ክን​ድህ የፊ​ት​ህም ብር​ሃን ነው እንጂ፤ ይቅር ብለ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና።


የኀ​ያ​ላን አም​ላክ አቤቱ፥ በባ​ሪ​ያህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈ​ጣ​ለህ?


የሕ​ዝ​ቤን ቅሬታ ከበ​ተ​ን​ኋ​ቸው ምድር ሁሉ ወደ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸው ሰብ​ስቤ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይበ​ዛሉ፤ ይባ​ዛ​ሉም።


ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓል የሚ​መጣ የለ​ምና የጽ​ዮን መን​ገ​ዶች አለ​ቀሱ፤ በሮ​ችዋ ሁሉ ፈር​ሰ​ዋል፤ ካህ​ና​ቷም ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ደና​ግ​ሎ​ች​ዋም ተማ​ረኩ፤ እር​ስ​ዋም በም​ሬት አለች።


ዛይ። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቀድሞ ወድዳ በሠ​ራ​ችው ሥራ ሁሉ የመ​ከ​ራ​ዋን ወራት አሰ​በች፤ ሕዝ​ብዋ በአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች እጅ በወ​ደቀ ጊዜ፥ የሚ​ረ​ዳ​ትም በሌ​ላት ጊዜ፥ አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች አዩ​አት፤ በመ​ፍ​ረ​ስ​ዋም ሳቁ።


ከአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከሀ​ገ​ሮ​ችም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ገዛ ሀገ​ራ​ቸ​ውም አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች ላይ፥ በፈ​ሳ​ሾ​ችም አጠ​ገብ፥ በም​ድ​ርም ላይ ሰዎች በሚ​ኖ​ሩ​ባት ስፍራ ሁሉ አሰ​ማ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ከአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ ገዛ ምድ​ራ​ች​ሁም እመ​ል​ሳ​ች​ኋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በከ​ተ​ማ​ዪቱ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መካ​ከል እለፍ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም ስለ ተሠ​ራው ኀጢ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ለ​ቅ​ሱና በሚ​ተ​ክዙ ሰዎች ግን​ባር ላይ ምል​ክት ጻፍ አለው።


የይ​ሁዳ ልጆ​ችና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አንድ አለቃ ይሾ​ማሉ፤ ከም​ድ​ሪ​ቱም ይወ​ጣሉ፤ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ቀን ታላቅ ይሆ​ና​ልና።


በዓ​መት በዓል ቀንና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ቀን ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?


በዚያ ዘመን አስገባችኋለሁ፥ በዚያም ዘመን እሰበስባችኋለሁ፣ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር አሕዛብ ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


跟着我们:

广告


广告