Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘካርያስ 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እነሆ፥ ጌታ ይገፍፋታል፥ በባሕርም ላይ ያለውን ብርታትዋን ይመታል፣ እርስዋም በእሳት ትበላለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ጌታ ግን ሀብቷን ይወስዳል፤ በባሕር ያላትንም ኀይል ይደምስሳል፤ እርሷም በእሳት ፈጽማ ትጠፋለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እነሆ፥ ጌታ ሀብቷን ይገፍፋታል፥ ወደ ባሕርም ውስጥ ያሰምጠዋል፤ እርሷም በእሳት ትበላለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ነገር ግን የሰበሰበችውን ሁሉ እግዚአብሔር ይወስድባታል፤ ሀብትዋን ወደ ባሕር ይጥለዋል፤ ከተማይቱም በእሳት ተቃጥላ ዐመድ ትሆናለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እነሆ፥ ጌታ ይገፍፋታል፥ በባሕርም ላይ ያለውን ብርታትዋን ይመታል፥ እርስዋም በእሳት ትበላለች።

参见章节 复制




ዘካርያስ 9:4
14 交叉引用  

የሀብት ድልብ ለኃጥኣን አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች።


በቍጣ ቀን ገንዘብ አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች። ጻድቅ በሞተ ጊዜ ጸጸትን ይተዋል፥ የኀጢአተኛ ሞት ግን በእጅ የተያዘና ሣቅ ይሆናል።


ነገ​ሥ​ታ​ቱን ያበ​ሳ​ጨ​ቻ​ቸው የባ​ሕር ሰዎች እጃ​ቸው ትደ​ክ​ማ​ለች፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ነ​ዓ​ንን ኀይል ያጠፉ ዘንድ አዘዘ።


በአ​ን​ቺም ላይ ሙሾ ያሞ​ሻሉ፤ እን​ዲ​ህም ይሉ​ሻል፦ በባ​ሕር የተ​ቀ​መ​ጥሽ፥ በባ​ሕ​ርም ውስጥ የጸ​ናሽ፥ ከሚ​ቀ​መ​ጡ​ብ​ሽም ጋር በዙ​ሪ​ያሽ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ያስ​ፈ​ራሽ፥ የከ​በ​ርሽ ከተማ ሆይ! እን​ዴት ጠፋሽ!


በን​ግ​ድ​ህም ብዛት ግፍ በው​ስ​ጥህ ተሞላ፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ሠራህ፤ ስለ​ዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ጣል​ሁህ፤ የም​ት​ጋ​ርድ ኪሩብ ሆይ! ከእ​ሳት ድን​ጋ​ዮች መካ​ከል አጠ​ፋ​ሁህ።


በበ​ደ​ልህ ብዛት፥ በን​ግ​ድ​ህም ኀጢ​አት መቅ​ደ​ስ​ህን አረ​ከ​ስህ፤ ስለ​ዚህ እሳ​ትን ከው​ስ​ጥህ አው​ጥ​ቻ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም በል​ታ​ሃ​ለች፤ በሚ​ያ​ዩ​ህም ሁሉ ፊት በም​ድር ላይ አመድ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።


“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢ​ሮ​ስን አለቃ እን​ዲህ በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ልብህ ኰር​ት​ዋል፥ አንተ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕር መካ​ከል እን​ዲ​ቀ​መጥ እኔም ተቀ​ም​ጫ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤ አንተ ሰው ስት​ሆን ልብ​ህን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ ብታ​ደ​ር​ግም አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።


ወደ ጕድ​ጓድ ያወ​ር​ዱ​ሃል፤ በሰ​ይ​ፍም ትሞ​ታ​ለህ፤ ሬሳ​ህ​ንም ወደ ባሕር ይጥ​ሉ​ታል።


ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን በይ​ሁዳ ልጆች እጅ እሸ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ለሩ​ቆቹ ሕዝብ በም​ርኮ ይሸ​ጡ​አ​ች​ኋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


በጢ​ሮስ ቅጥር ላይ እሳ​ትን አሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋ​ንም ትበ​ላ​ለች።”


አስቀሎና አይታ ትፈራለች፣ ጋዛ ደግሞ አይታ እጅግ ትታመማለች፣ አቃሮንም እንዲሁ፥ ተስፋዋ ይቈረጣልና፣ ንጉሡም ከጋዛ ይጠፋል፥ በአስቀሎናም የሚቀመጥ አይገኝም።


跟着我们:

广告


广告