Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘካርያስ 14:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ይሆናሉ፣ የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ ከእነዚያም ወስደው ይቀቅሉባቸዋል፣ በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቤት ከነዓናዊው ከእንግዲህ ወዲያ አይገኝም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶች ሁሉ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ይሆናሉ፤ መሥዋዕት ለማቅረብ የሚመጡ ሁሉ ምንቸቶቹን በመውሰድ ያበስሉባቸዋል፤ በዚያ ቀን በእግዚአብሔር ጸባኦት ቤት ከእንግዲህ ወዲያ ከነዓናዊ አይገኝም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ የተቀደሱ ይሆናሉ። የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ፥ በእነርሱም ውስጥ ይቀቅሉባቸዋል። በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ ቤት ከእንግዲህ ወዲያ ነጋዴ አይገኝም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምድር የሚገኘው ማሰሮ ሁሉ ለሠራዊት አምላክ የተለየ ይሆናል፤ መሥዋዕት የሚያቀርቡ ሰዎች ሁሉ በማሰሮዎቹ ጥቂቱን የመሥዋዕቱን ሥጋ ያበስሉባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መቅደስ ውስጥ የሚነግድ ማንም ሰው አይኖርም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ይሆናሉ፥ የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ ከእነዚያም ወስደው ይቀቅሉባቸዋል፥ በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቤት ከነዓናዊው ከእንግዲህ ወዲያ አይገኝም።

参见章节 复制




ዘካርያስ 14:21
27 交叉引用  

እር​ሱም፥ “ሂዱ፤ የሰ​ባ​ው​ንም ብሉ፤ ጣፋ​ጩ​ንም ጠጡ፤ ለእ​ነ​ዚ​ያም ምንም ለሌ​ላ​ቸው እድል ፈን​ታ​ቸ​ውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌ​ታ​ችን የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ላ​ችን ነውና አት​ዘኑ” አላ​ቸው።


በዚ​ያም ንጹሕ መን​ገድ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም የተ​ቀ​ደሰ መን​ገድ ይባ​ላል፤ በዚ​ያም ንጹ​ሓን ያል​ሆኑ አያ​ል​ፉ​በ​ትም፤ ርኩስ መን​ገ​ድም በዚያ አይ​ኖ​ርም፤ የተ​በ​ተ​ኑ​ትም በእ​ርሱ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ሳ​ሳ​ቱ​ምም።


በጽ​ዮን የቀሩ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ረፉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሕ​ይ​ወት የተ​ጻፉ ሁሉ፥ ቅዱ​ሳን ይባ​ላሉ።


ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፤ ጽዮን ሆይ፥ ኀይ​ል​ሽን ልበሺ፤ አን​ቺም ቅድ​ስ​ቲቱ ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘና ርኩስ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ወደ አንቺ አያ​ል​ፍ​ምና ክብ​ር​ሽን ልበሺ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ከአ​ሉት ሁሉ በል​ቡና በሥ​ጋው ያል​ተ​ገ​ረዘ የባ​ዕድ ልጅ እን​ግዳ ሁሉ ወደ መቅ​ደሴ አይ​ግባ።


“ርስ​ትም አድ​ር​ጋ​ችሁ ምድ​ርን በዕጣ በም​ታ​ካ​ፍ​ሉ​በት ጊዜ ከም​ድር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን የዕጣ ክፍል መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፤ በዳ​ር​ቻው ሁሉ ዙሪ​ያው የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል።


ስለ​ዚህ ወደ አም​ላ​ክህ ተመ​ለስ፤ ምሕ​ረ​ት​ንና ፍር​ድን ጠብቅ፤ ዘወ​ት​ርም ወደ አም​ላ​ክህ ቅረብ።


“እኔም በተ​ቀ​ደሰ ተራ​ራዬ በጽ​ዮን የም​ቀ​መጥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ያን ጊዜም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​ደ​ሰች ከተማ ትሆ​ና​ለች፥ እን​ግ​ዶ​ችም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ል​ፉ​ባ​ትም።


እናንተ በመክቴሽ የምትኖሩ ሆይ፥ የከነዓን ሕዝብ ሁሉ ጠፍተዋልና፥ ብርም የተሸከሙ ሁሉ ተቈርጠዋልና አልቅሱ።


በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኵራ ላይ፦ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ተብሎ ይጻፋል፣ በእግዚአብሔርም ቤት ያሉ ምንቸቶች በመሠዊያው ፊት እንዳሉ ዳካዎች ይሆናሉ።


በምትበሉበትና በምትጠጡበትስ ጊዜ፥ ለራሳችሁ የምትበሉና የምትጠጡ አይደላችሁምን?


ብት​በ​ሉም፥ ብት​ጠ​ጡም የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር አድ​ር​ጉት።


እና​ን​ተም፥ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ች​ሁም፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ክፍ​ልና ርስት ስለ​ሌ​ለው በደ​ጆ​ቻ​ችሁ ውስጥ የተ​ቀ​መ​ጠው ሌዋ​ዊም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


በዚ​ያም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ብሉ፤ እጃ​ች​ሁ​ንም በም​ት​ዘ​ረ​ጉ​በት፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ረ​ካ​ችሁ ነገር ሁሉ፥ እና​ን​ተና ቤተ​ሰ​ባ​ችሁ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።


ክር​ስ​ቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታ​መነ ነው፤ እኛም የም​ን​ደ​ፍ​ር​በ​ትን፥ የም​ን​መ​ካ​በ​ት​ንም ተስፋ እስከ መጨ​ረ​ሻው አጽ​ን​ተን ብን​ጠ​ብቅ ቤቱ ነን።


ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?


ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኵሰትና ውሸትም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም።


ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።


跟着我们:

广告


广告