Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘካርያስ 11:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እኔም፦ እናንተን አልጠብቅም፣ የሚሞተው ይሙት፥ የሚጠፋውም ይጥፋ፣ የቀረውም እያንዳንዱ የባልንጀራውን ሥጋ ይብላ አልሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “እረኛችሁ አልሆንም፤ የሚሞቱት ይሙቱ፤ የሚጠፉት ይጥፉ፤ የቀሩትም አንዱ የሌላውን ሥጋ ይብላ” አልኋቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እኔም፦ “እናንተን አልጠብቅም፤ የሚሞተው ይሙት፥ የሚጠፋውም ይጥፋ፤ የቀሩትም እርስ በእርሳቸው ተበላልተው ይጨራረሱ።” አልሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚህ በኋላ መንጋውን እንዲህ አልኩ፦ “እኔ ከእንግዲህ ወዲህ እረኛችሁ አልሆንም፤ የሚሞቱት ይሙቱ፤ የሚጠፉትም ይጥፉ፤ የተረፉትም እርስ በርሳቸው ተባልተው ይለቁ፤”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እኔም፦ እናንተን አልጠብቅም፥ የሚሞተው ይሙት፥ የሚጠፋውም ይጥፋ፥ የቀረውም እያንዳንዱ የባልንጀራውን ሥጋ ይብላ አልሁ።

参见章节 复制




ዘካርያስ 11:9
22 交叉引用  

የወ​ን​ዶ​ችና የሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሥጋ አበ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ውን የሚ​ሹት በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው ጭን​ቀ​ትና መከ​በብ የባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ሥጋ ይበ​ላሉ።


ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ምን​ድር ነው?” ብሎ ቢጠ​ይ​ቅህ፥ አንተ፥ “ሸክሙ እና​ንተ ናችሁ፤ እጥ​ላ​ች​ሁ​ማ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


ስለ​ዚህ፥ እነሆ- ፈጽሜ እረ​ሳ​ች​ኋ​ለሁ እና​ን​ተ​ንም፥ ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም የሰ​ጠ​ኋ​ትን ከተማ ከፊቴ አን​ሥቼ እጥ​ላ​ለሁ።


መጥ​ቶም የግ​ብ​ፅን ምድር ይመ​ታል፤ ለሞ​ትም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሞት፥ ለም​ር​ኮም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለም​ርኮ፥ ለሰ​ይ​ፍም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሰ​ይፍ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።


ስለ​ዚህ በመ​ካ​ከ​ልሽ አባ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ፤ ልጆ​ችም አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ፤ ፍር​ድ​ንም አደ​ር​ግ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ከአ​ን​ቺም የቀ​ረ​ውን ሁሉ ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ለሁ።


ሕዝቤ አእ​ምሮ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ይመ​ስ​ላሉ፤ አን​ተም አእ​ም​ሮህ ተለ​ይ​ቶ​ሃ​ልና እኔ ካህን እን​ዳ​ት​ሆ​ነኝ እተ​ው​ሃ​ለሁ፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ሕግ ረስ​ተ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ልጆ​ች​ህን እረ​ሳ​ለሁ።


በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።


ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ፤” አለ።


በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና “ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ፤” አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።


ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች፤ ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ ገና ለጥ​ቂት ጊዜ ብር​ሃን ከእ​ና​ንተ ጋር ነው፤ በጨ​ለማ የሚ​መ​ላ​ለስ የሚ​ሄ​ድ​በ​ትን አያ​ው​ቅ​ምና ጨለማ እን​ዳ​ያ​ገ​ኛ​ችሁ ብር​ሃን ሳለ​ላ​ችሁ ተመ​ላ​ለሱ፤


ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “እኔ እሄ​ዳ​ለሁ ትሹ​ኛ​ላ​ች​ሁም፤ ነገር ግን አታ​ገ​ኙ​ኝም፤ በኀ​ጢ​ኣ​ታ​ች​ሁም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በ​ትም እና​ንተ መም​ጣት አይ​ቻ​ላ​ች​ሁም” አላ​ቸው።


እነሆ፥ በኀ​ጢ​ኣ​ታ​ችሁ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ እን​ዳ​ል​ኋ​ችሁ፥ እኔ እንደ ሆንሁ ባታ​ምኑ በኀ​ጢ​ኣ​ት​ችሁ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።”


ዐመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፤ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፤ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፤ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ፤” አለ።


跟着我们:

广告


广告