本书并非出自上帝启示,且不属于基督教正典或犹太教塔纳赫的一部分。仅为历史与研究目的而展示。 查看完整说明 መጽሐፈ ጦቢት 3:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 አሁንም በፊትህ ደስ የሚያሰኝህን በእኔ አድርግ፤ ከመኖር መሞት ይሻለኛልና በሞት እሰናበት ዘንድ፥ መሬትም እሆን ዘንድ ነፍሴን የሚቀበላትን እዘዝልኝ። በሐሰትና በውርደት ተግዳሮትን ሰምቻለሁና፥ ኀዘንም በእኔ ላይ በዝትዋልና ከመከራዬ እሰናበት ዘንድ፥ ወደ ዘለዓለማዊ ቦታም እሄድ ዘንድ እዘዝ፤ ፊትህንም ከእኔ አትመልስ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 አሁንም እንደ ፈቀድህ አድርገኝ፤ ከዚህች ምድር ተላቅቄ ዳግም አፈር ልሁን፥ ከመኖር መሞት ይሻለኛልና፥ ከንቱ ስድብን ተቋቁሜአልሁና፥ በታላቅ ኃዘንም ውስጥ ነኝ፤ ጌታ ሆይ ከዚህ መከራ እንድላቀቅ እዘዝ፥ ወደ ዘላለማዊ ቤቴም እንድሄድ ፍቀድ፤ ጌታ ሆይ ፊትህን ከኔ አትመልስ፤ በማያባራ ሰቆቃ ከተሞላ ሕይወት ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ፥ ከዚህ ወዲያ ስድቦችን መሸከም አልችልም።” 参见章节 |