Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ቲቶ 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አንተን በቀርጤስ የተውሁህ ገና ያልተስተካከለውን ነገር እንድታስተካክልና ባዘዝሁህ መሠረት በየከተማው ሽማግሌዎችን እንድትሾም ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የተቀረውን ሥራ እንድታቃናና በየከተማው እኔ እንዳዘዝሁህ ሽማግሌዎችን እንድትሾም፥ አንተን በዚህ ምክንያት በቀርጤስ ተውሁህ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አንተን በቀርጤስ የተውኩበት ምክንያት ያልተስተካከለውን እንድታስተካክልና ባዘዝኩህም መሠረት የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን በየከተማው እንድትሾም ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤

参见章节 复制




ቲቶ 1:5
18 交叉引用  

ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እስ​ኪ​ሠራ ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ማደ​ሪያ ፊት በበ​ገና እያ​ዜሙ ያገ​ለ​ግሉ ነበር፤ በየ​ተ​ራ​ቸ​ውም ለአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ይቆሙ ነበር።


ሰባ​ኪ​ውም ጠቢብ ስለ ሆነ ለሕ​ዝቡ ዕው​ቀ​ትን አስ​ተ​ማረ፥ ጆሮ​ውም እን​ቆ​ቅ​ል​ሽን መረ​መረ።


እንደ እኔ ያለ አዳኝ ማን ነው? ይነ​ሣና ይጥራ፤ ይና​ገ​ርም፤ ሰውን ከፈ​ጠ​ር​ሁ​በት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለሙ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያዘ​ጋ​ጅ​ልኝ፤ የሚ​መ​ጣ​ውም ነገር ሳይ​ደ​ርስ ይና​ገር።


በእ​ነ​ዚ​ያም ድን​ጋ​ዮች ስፍራ ሌሎች ድን​ጋ​ዮ​ችን ያገ​ባሉ፤ ሌላም ጭቃ ወስ​ደው ቤቱን ይመ​ር​ጉ​ታል።


እን​ደ​ዚ​ህም አድ​ር​ገው በበ​ር​ና​ባ​ስና በሳ​ውል እጅ ወደ ቀሳ​ው​ስት ላኩት።


ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ቀሳ​ው​ስ​ትን ሾሙ፤ ጾሙ፤ ጸለ​ዩም፤ ለሚ​ታ​መ​ኑ​በት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አደራ ሰጡ​አ​ቸው።


ከቀ​ር​ጤ​ስና ከዐ​ረ​ብም የመ​ጣን፥ እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጌት​ነት በየ​ሀ​ገ​ራ​ችን ቋንቋ ሲና​ገሩ እን​ሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለን።”


ያም ወደብ ክረ​ም​ቱን ሊከ​ር​ሙ​በት የማ​ይ​መች ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ብዙ​ዎች ከዚያ ይወጡ ዘንድ ይቻ​ላ​ቸው እንደ ሆነ በቀኝ በኩል ወደ አለው ፊንቄ ወደ​ሚ​ባ​ለው ወደ ሁለ​ተ​ኛው የቀ​ር​ጤስ ወደብ ይደ​ርሱ ዘንድ ወደዱ።


ልከኛ የአ​ዜብ ነፋ​ስም ነፈሰ፤ እነ​ር​ሱም እንደ ወደዱ የሚ​ደ​ርሱ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር፤ መል​ሕ​ቁ​ንም አነሡ፤ በቀ​ር​ጤ​ስም አጠ​ገብ ሄዱ።


ከእ​ኛም መብል የበላ አል​ነ​በ​ረም። ጳው​ሎ​ስም ተነ​ሥቶ በመ​ካ​ከል ቆመና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰዎች ሆይ፥ ቀድሞ ቃሌን ሰም​ታ​ች​ሁኝ ቢሆን ከቀ​ር​ጤ​ስም ባት​ወጡ ኖሮ ከዚህ ጕዳ​ትና መከራ በዳ​ና​ችሁ ነበር።


ብዙ ቀንም እያ​ዘ​ገ​ምን ሄድን፤ በጭ​ን​ቅም ወደ ቀኒ​ዶስ አን​ጻር ደረ​ስን፤ ወደ​ዚ​ያም በቀ​ጥታ ለመ​ድ​ረስ ነፋስ ቢከ​ለ​ክ​ለን በቀ​ር​ጤስ በኩል በሰ​ል​ሙና ፊት ለፊት ዐለ​ፍን።


መሰ​ብ​ሰ​ባ​ችሁ ለፍዳ እን​ዳ​ይ​ሆን፥ የተ​ራበ ቢኖር በቤቱ ይብላ፤ አት​ነ​ቃ​ቀ​ፉም፤ ሌላ​ውን ሥር​ዐት ግን መጥቼ እሠ​ራ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ነገር ግን ሁሉን በአ​ገ​ባ​ብና በሥ​ር​ዐት አድ​ርጉ፤


ስለ​ዚ​ህም በየ​ስ​ፍ​ራው በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ርሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ የሄ​ድ​ሁ​በ​ትን መን​ገድ ይገ​ል​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መ​ነና ልጄ ወዳጄ የሆነ ጢሞ​ቴ​ዎ​ስን ልኬ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


እኔ በሥጋ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ባል​ኖ​ርም እን​ኳን፥ በመ​ን​ፈስ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝ፤ እነሆ ጠባ​ያ​ች​ሁ​ንና ሥር​ዐ​ታ​ች​ሁን፥ በክ​ር​ስ​ቶ​ስም ያለ የእ​ም​ነ​ታ​ች​ሁን ጽናት ስለ አየሁ ደስ ይለ​ኛል።


ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና፤ በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት አይጠቅሙም።


ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ።


የገዛ ራሳቸው ነቢይ የሆነ ከእነርሱ አንዱ “የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፥ ክፉዎች አራዊት፥ በላተኞች፥ ሥራ ፈቶች ናቸው፤” ብሎአል።


跟着我们:

广告


广告