ማሕልየ መሓልይ 8:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 በልጅ ወንድምዋ ላይ ተደግፋ እንደ ማለዳ ደምቃና አብርታ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ከእንኮይ በታች አስነሣሁህ፤ በዚያ እናትህ አማጠችህ፥ በዚያም ወላጅ እናትህ ወለደችህ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ውዷን ተደግፋ፣ ከምድረ በዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ከእንኮይ ዛፍ ሥር አስነሣሁህ፤ በዚያ እናትህ ፀነሰችህ፤ በዚያም ታምጥ የነበረችው አንተን ወለደችህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 በውድዋ ላይ ተደግፋ ከምድረበዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ከእንኮይ በታች አስነሣሁህ፥ በዚያ እናትህ ወለደችህ፥ በዚያም ወላጅ እናትህ አማጠችህ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 በወዳጅዋ ትከሻ ላይ ደገፍ ብላ ከበረሓ የምትመጣ ይህች ማን ናት? ዱሮ እናትህ አንተን አምጣ በወለደችበት በፖም ዛፍ ሥር ቀስቅሼ አስነሣሁህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 በውድዋ ላይ ተደግፋ ከምድረ በዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ከእንኮይ በታች አስነሣሁህ፥ በዚያ እናትህ ወለደችህ፥ በዚያም ወላጅ እናትህ አማጠችህ። 参见章节 |