Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 6:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥ ከአ​ንቺ ጋር እን​ፈ​ል​ገው ዘንድ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ወዴት ሄደ? ልጅ ወን​ድ​ም​ሽስ ወዴት ፈቀቅ አለ?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ ውድሽ ወዴት ሄደ? ዐብረንሽም እንድንፈልገው፣ ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ውድሽ ወዴት ሄደ? አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፥ ከአንቺ ጋር እንፈልገው ውድሽ ወዴት ፈቀቅ አለ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ! ወዳጅሽ ወዴት ሄደ? እኛም አብረንሽ እንድንፈልገው የሄደበትን አቅጣጫ ንገሪን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከአንቺ ጋር እንፈልገው ዘንድ ውድሽ ወዴት ሄደ? ውድሽስ ወዴት ፈቀቅ አለ?

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 6:1
13 交叉引用  

ከወደ ኋላ​ህም ሳቡህ፥ በሽ​ቱህ መዓ​ዛም እን​ሮ​ጣ​ለን፤ ንጉሡ ወደ እል​ፍኙ አገ​ባኝ፤ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ኛል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ ከወ​ይን ጠጅ ይልቅ ጡቶ​ች​ሽን እን​ወ​ዳ​ለን፤ አን​ቺ​ንም መው​ደድ የተ​ገባ ነው።


አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥ ያላ​ወ​ቅሽ እንደ ሆነ የመ​ን​ጎ​ችን ፍለጋ ተከ​ት​ለሽ ውጪ፥ የፍ​የል ግል​ገ​ሎ​ች​ሽ​ንም በእ​ረ​ኞች ድን​ኳ​ኖች አጠ​ገብ አሰ​ማሪ።


በእ​ሾህ መካ​ከል እን​ዳለ የሱፍ አበባ፥ እን​ዲሁ ወዳጄ በቈ​ነ​ጃ​ጅት መካ​ከል ነሽ።


ለልጅ ወን​ድሜ ከፈ​ት​ሁ​ለት፥ ልጅ ወን​ድሜ ግን ሂዶ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተ​ነሣ ደነ​ገ​ጠች፤ ፈለ​ግ​ሁት፥ አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም፤ ጠራ​ሁት፥ አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም።


አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥ ከወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ማን ነው? ይህን ያህል መሐላ አም​ለ​ሽ​ና​ልና ከወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ማን ነው?


ወዳጄ ሆይ፥ እንደ ቴርሳ ውብ ነሽ፥ እንደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ያማ​ርሽ ነሽ፤ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰ​ለፈ ሠራ​ዊት ታስ​ፈ​ር​ያ​ለሽ።


አሁ​ንም የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ሃን እን​መ​ላ​ለስ።


ጌታ ሆይ! አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ ነህ፤ በመ​ከ​ራም ጊዜ ታድ​ነ​ዋ​ለህ፤ በም​ድር እንደ እን​ግዳ፥ ወደ ማደ​ሪ​ያም ዘወር እን​ደ​ሚል መን​ገ​ደኛ ስለ ምን ትሆ​ና​ለህ?


እግዚአብሔር እንደ ሥራሽ ይስጥሽ፣ ከክንፉም በታች መጠጊያ እንድታገኚ በመጣሽበት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ደመወዝሽ ፍጹም ይሁን አላት።


跟着我们:

广告


广告