Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እኔ ተኝቼ ነበር፥ ልቤ ግን ነቅታ ነበር፤ ልጅ ወን​ድሜ ቃል ደጅ እየ​መታ መጣ፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደ​ም​ደ​ሚ​ያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቍ​ን​ዳ​ላ​ዬም የሌ​ሊት ነጠ​ብ​ጣብ ሞል​ቶ​በ​ታ​ልና ክፈ​ች​ልኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል፤ ስሙ! ውዴ በር ያንኳኳል፤ እንዲህ ይላል፤ “እኅቴ ወዳጄ፣ ርግቤ፣ አንቺ እንከን የሌለብሽ፤ ክፈቺልኝ። ራሴ በጤዛ፣ ጠጕሬም በሌሊቱ ርጥበት ረስርሷል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፥ የውዴ ድምፅ ነው፥ እርሱም ያንኳኳል፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ፥ ራሴ በጠል፥ ጸጉሬም በሌሊት ነጠብጣብ ርሶአል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እኔ ተኝቼአለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ ውዴ እንዲህ እያለ በር ሲያንኳኳ ሰማሁት፤ “ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ! እንከን የሌለብሽ ርግቤ ሆይ! እባክሽ በሩን ክፈችልኝ፤ ራሴ በጠል ርሶአል ጠጒሬም በሌሊት ካፊያ ረስርሶአል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፥ የውዴ ቃል ነው፥ እርሱም ደጁን ይመታል፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቈንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 5:2
39 交叉引用  

ያዕ​ቆ​ብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይወ​ድ​ዳት ስለ​ነ​በረ በእ​ርሱ ዘንድ ጥቂት ቀን ሆነ​ለት።


አቤቱ፥ በተ​ጨ​ነ​ቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ሰማ​ኸ​ኝም።


ልጄ ሆይ፥ ልብህን ስጠኝ፥ ዐይኖችህም መንገዴን ይጠብቁ።


ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ውብ ነህ፥ መልከ መል​ካ​ምም ነህ፤ አል​ጋ​ች​ንም ለም​ለም ነው።


ልጅ ወን​ድሜ እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ልኝ፦ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፥ መል​ካ​ምዋ ርግቤ ሆይ፥ ነዪ።


ፊት​ህን አሳ​የኝ፥ ቃል​ህ​ንም አሰ​ማኝ፤ ቃልህ ያማረ፥ ፊት​ህም የተ​ዋበ ነውና።


እነሆ፥ የልጅ ወን​ድሜ ቃል በተ​ራ​ሮች ላይ ሲዘ​ልል፥ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ሲወ​ረ​ወር ይመ​ጣል።


ሌሊት በም​ን​ጣፌ ላይ ነፍሴ የወ​ደ​ደ​ች​ውን ፈለ​ግ​ሁት፤ ፈለ​ግ​ሁት አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም። ጠራ​ሁት አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም።


ወዳጄ ሆይ፥ ሁለ​ን​ተ​ናሽ ውብ ነው፥ ምንም ነውር የለ​ብ​ሽም።


እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ልቤን ማረ​ክ​ሽው፤ አንድ ጊዜ በዐ​ይ​ኖ​ችሽ፥ ከአ​ን​ገ​ት​ሽም ድሪ በአ​ንዱ፥ ልቤን ማረ​ክ​ሽው።


ራሱ ምዝ​ምዝ ወርቅ ነው፤ ቈን​ዳ​ላው የተ​ዝ​ረ​ፈ​ረፈ ነው፥ እንደ ቍራ ጥቍ​ረ​ትም ጥቁር ነው።


ለልጅ ወን​ድሜ ከፈ​ት​ሁ​ለት፥ ልጅ ወን​ድሜ ግን ሂዶ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተ​ነሣ ደነ​ገ​ጠች፤ ፈለ​ግ​ሁት፥ አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም፤ ጠራ​ሁት፥ አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም።


ርግቤ መደ​ም​ደ​ሚ​ያ​ዬም አን​ዲት ናት፤ ለእ​ናቷ አን​ዲት ናት፥ ለወ​ለ​ደ​ቻ​ትም የተ​መ​ረ​ጠች ናት። ቈነ​ጃ​ጅ​ትም አይ​ተው አሞ​ገ​ሱ​አት፥ ንግ​ሥ​ታ​ትና ቁባ​ቶ​ችም አመ​ሰ​ገ​ኑ​አት።


ወደ ዘን​ባ​ባው ዛፍ እወ​ጣ​ለሁ ጫፉ​ንም እይ​ዛ​ለሁ አልሁ፤ ጡቶ​ችሽ እንደ ወይን ዘለላ ናቸው፥ የአ​ፍ​ን​ጫ​ሽም ሽታ እንደ እን​ኮይ ነው።


ብዙ ውኃ ፍቅ​ርን ያጠ​ፋት ዘንድ አይ​ች​ልም፥ ፈሳ​ሾ​ችም አያ​ሰ​ጥ​ሙ​አ​ትም፤ ሰው የቤ​ቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ አይ​ን​ቁ​ትም።


ጀር​ባ​ዬን ለግ​ር​ፋት፥ ጕን​ጬ​ንም ለጽ​ፍ​ዐት ሰጠሁ፤ ፊቴ​ንም ከም​ራቅ ኀፍ​ረት አል​መ​ለ​ስ​ሁም።


ፊቱ ከሰ​ዎች ሁሉ ይልቅ፥ መል​ኩም ከሰ​ዎች ልጆች ይልቅ ያለ ክብር ነውና ብዙ ሰዎች ስለ እርሱ ያደ​ን​ቃሉ፤


ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ተመልሶ ከእንቅልፋ እንደሚነቃ ሰው አነቃኝ።


የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልገውም ያገኛል፤ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።


ማለዳም ተነሥቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ፤ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ።


ፈራ፤ መላ​ል​ሶም ጸለየ፤ ላቡም በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ ደም ነጠ​ብ​ጣብ ሆነ።


በዚ​ያም ወራት ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊ​ቱን ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልይ ነበር፤


ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ት​ንም ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው በእ​ን​ቅ​ልፍ ፈዝ​ዘው አገኘ፤ በነ​ቁም ጊዜ ክብ​ሩ​ንና ከእ​ርሱ ጋር ቆመው የነ​በ​ሩ​ትን ሁለት ሰዎች አዩ።


ሁሉ​ንም አው​ጥቶ ባሰ​ማ​ራ​ቸው ጊዜ በፊት በፊ​ታ​ቸው ይሄ​ዳል፤ በጎ​ቹም ይከ​ተ​ሉ​ታል፤ ቃሉን ያው​ቃ​ሉና።


ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋርም ተሰ​ቀ​ልሁ፤ ሕይ​ወ​ቴም አለ​ቀች፤ ነገር ግን በክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወት አለሁ፤ ዛሬም በሥ​ጋዬ የም​ኖ​ረ​ውን ኑሮ የወ​ደ​ደ​ኝን ስለ እኔም ራሱን አሳ​ልፎ የሰ​ጠ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ በማ​መን እኖ​ራ​ለሁ።


“የተ​ኛህ ንቃ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይ​ተህ ተነሥ፤ ክር​ስ​ቶ​ስም ያበ​ራ​ል​ሃል” ብሎ​አ​ልና።


ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።


እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።


ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፤ የተገባቸውም ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።


跟着我们:

广告


广告