ማሕልየ መሓልይ 5:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ጕሮሮው እጅግ ጣፋጭ ነው፥ ሁለንተናውም የተወደደ ነው፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ልጅ ወንድሜ ይህ ነው፥ ወዳጄም ይህ ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 አፉ ራሱ ጣፋጭ ነው፤ ሁለንተናውም ያማረ ነው። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ ውዴ ይህ ነው፤ ባልንጀራዬም እርሱ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፥ እርሱም ፈጽሞ ያማረ ነው፥ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ባልንጀራዬም ይህ ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 አፉ እንደ ማር. የጣፈጠ ነው፤ ሁለንተናውም የደስ ደስ አለው፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት እንግዲህ ውዴና ወዳጄ ይህን የመሰለ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፥ እርሱም ፈጽሞ ያማረ ነው፥ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ባልንጀራዬም ይህ ነው። 参见章节 |