Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 5:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እግ​ሮቹ በም​ዝ​ምዝ ወርቅ እንደ ተመ​ሠ​ረቱ እንደ ዕብነ በረድ ምሰ​ሶ​ዎች ናቸው፤ መልኩ እንደ ሊባ​ኖ​ስና እንደ ዝግባ ዛፍ የተ​መ​ረጠ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እግሮቹ በንጹሕ ወርቅ መቆሚያ ላይ የተተከሉ፣ የዕብነ በረድ ምሰሶዎችን ይመስላሉ፤ መልኩ እንደ ሊባኖስ ነው፤ እንደ ዝግባ ዛፎቹም ምርጥ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እግሮቹ በምዝምዝ ወርቅ ላይ የተመሠረቱ የዕብነ በረድ ምሰሶች ናቸው፥ መልኩ እንደ ሊባኖስ፥ እንደ ዝግባ ዛፍ ምርጥ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እግሮቹ በወርቅ መሠረት ላይ የተተከሉ የዕብነበረድ ምሰሶዎችን ይመስላሉ፤ መልኩ በሊባኖስ ዛፍ እንዳጌጠ እንደ ሊባኖስ ተራራ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እግሮቹ በምዝምዝ ወርቅ እንደ ተመሠረቱ እንደ ዕብነ በረድ ምሰሶች ናቸው፥ መልኩ እንደ ሊባኖስና እንደ ዝግባ ዛፍ መልካም ነው።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 5:15
19 交叉引用  

ስለ ዛፍም ከሊ​ባ​ኖስ ዝግባ ጀምሮ በቅ​ጥር ግንብ ላይ እስ​ከ​ሚ​በ​ቅ​ለው እስከ አሽ​ክት ድረስ ይና​ገር ነበር፤ ደግ​ሞም ስለ አው​ሬ​ዎ​ችና ስለ ወፎች ስለ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችና ስለ ዓሣ​ዎች ይና​ገር ነበር።


ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሁህ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝና፤ አፍ​ህን አስፋ፥ እሞ​ላ​ዋ​ለ​ሁም።


ከሃ​ያ​ውም ሳን​ቆች በታች አርባ የብር እግ​ሮ​ችን አድ​ርግ፤ ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሳንቃ በታች ለሁ​ለት ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ሁለት እግ​ሮች ይሁኑ። ከሌ​ላ​ውም ሳንቃ በታች ለሁ​ለት ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ሁለት እግ​ሮች ይሁኑ።


ፊት​ህን አሳ​የኝ፥ ቃል​ህ​ንም አሰ​ማኝ፤ ቃልህ ያማረ፥ ፊት​ህም የተ​ዋበ ነውና።


ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ከከ​ን​ፈ​ሮ​ችሽ የማር ወለላ ይን​ጠ​ባ​ጠ​ባል፤ ከም​ላ​ስ​ሽም በታች ማርና ወተት አለ፥ የል​ብ​ስ​ሽም መዓዛ እንደ ዕጣን መዓዛ ነው።


ሁለቱ ጡቶ​ችሽ እንደ ሁለት መንታ እንደ ሚዳቋ ግል​ገ​ሎች ናቸው።


ዛይ። ቅዱ​ሳ​ኖ​ችዋ ከበ​ረድ ይልቅ ነጡ፤ ከወ​ተ​ትም ይልቅ ነጡ፤ በመ​ው​ጣ​ታ​ቸ​ውም ሰን​ፔር ከሚ​ባል ዕንቍ ይልቅ ፈጽ​መው ቀሉ።


ከፍ ባለው በእ​ስ​ራ​ኤል ተራራ ላይ እተ​ክ​ለ​ዋ​ለሁ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ች​ንም ያወ​ጣል፤ ፍሬም ያፈ​ራል፤ ታላ​ቅም ዝግባ ይሆ​ናል፤ በበ​ታ​ቹም ወፎች ሁሉ ያር​ፋሉ፤ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ቹም ጥላ በክ​ንፍ የሚ​በ​ርር ሁሉ ይጠ​ጋል፤ ቅር​ን​ጫ​ፉም ይሰ​ፋል።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት የነ​በሩ ዝግ​ባ​ዎች አይ​ተ​ካ​ከ​ሉ​ትም፥ ጥዶ​ችም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹን፥ አስታ የሚ​ባ​ለ​ውም ዛፍ ጫፎ​ቹን አይ​መ​ሳ​ሰ​ሉ​ትም ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ገነት ዛፍ ሁሉ በው​በቱ አይ​መ​ስ​ለ​ውም ነበር።


ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም ይዘ​ረ​ጋሉ፤ ውበ​ቱም እንደ ወይራ፥ ሽታ​ውም እንደ ሊባ​ኖስ ይሆ​ናል።


በጎነቱ እንዴት ታላቅ ነው! ውበቱስ እንዴት ታላቅ ነው! እህል ጐበዛዝቱን፥ ጉሽ ጠጅም ቈነጃጅቱን ያለመልማል።


በፊታቸውም ተለወጠ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።


መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ።


የሕ​ይ​ወ​ትን መን​ገድ አሳ​የ​ኸኝ፤ ከፊ​ትህ ጋራ ደስ​ታን አጠ​ገ​ብ​ኸኝ።


እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።


ሴቲ​ቱም ወደ ባልዋ መጥታ፥ “አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መል​ኩም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ እጅግ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ነበረ፤ ከወ​ዴ​ትም እንደ መጣ ጠየ​ቅ​ሁት፥ እር​ሱም ስሙን አል​ነ​ገ​ረ​ኝም።


跟着我们:

广告


广告