Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ልቤን ማረ​ክ​ሽው፤ አንድ ጊዜ በዐ​ይ​ኖ​ችሽ፥ ከአ​ን​ገ​ት​ሽም ድሪ በአ​ንዱ፥ ልቤን ማረ​ክ​ሽው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እኅቴ ሙሽራዬ፣ ልቤን ሰርቀሽዋል፤ በአንድ አፍታ እይታሽ፣ ከሐብልሽም በአንዱ ዕንቍ፣ ልቤን ሰርቀሽዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ልቤን በደስታ አሳበድሽው፥ አንድ ጊዜ በዐይኖችሽ፥ ከአንገትሽስ ድሪ በአንዱ ልቤን በደስታ አሳበድሽው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ፥ የዐይኖችሽ አመለካከትና የአንገትሽ ድሪ ልቤን ማርኮታል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ልቤን በደስታ አሳበድሽው፥ አንድ ጊዜ በዓይኖችሽ፥ ከአንገትሽስ ድሪ በአንዱ ልቤን በደስታ አሳበድሽው።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 4:9
31 交叉引用  

እር​ስ​ዋም ደግሞ በእ​ናቴ ወገን አይ​ደ​ለ​ችም እንጂ በእ​ው​ነት በአ​ባቴ ወገን እኅቴ ናት፤ ለእ​ኔም ሚስት ሆነች።


ፈር​ዖን ቀለ​በ​ቱን ከእጁ አወ​ለቀ፤ በዮ​ሴ​ፍም እጅ አደ​ረ​ገው፤ የነጭ ሐር ልብ​ስ​ንም አለ​በ​ሰው፤ በአ​ን​ገ​ቱም የወ​ርቅ ዝር​ግ​ፍን አደ​ረ​ገ​ለት፤


ከም​ድር ዳርቻ ጦር​ነ​ትን ይሽ​ራል፤ ቀስ​ትን ይሰ​ብ​ራል፥ ጋሻ​ንም ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፥ በእ​ሳ​ትም የጦር መሣ​ሪ​ያን ያቃ​ጥ​ላል።


ለራስህ የክብር ዘውድን ለአንገትህም የወርቅ ድሪ ታገኛለህና።


ውበቷ ድል አይንሣህ። በዐይኖችዋ አትጠመድ፥ በቅንድቧም አትማረክ።


ጕን​ጮ​ችሽ እንደ ዋኖስ እጅግ ያማሩ ናቸው፥ አን​ገ​ት​ሽም በዕ​ንቍ ድሪ ያማረ ነው።


ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤ ዐይ​ኖ​ች​ሽም እንደ ርግ​ቦች ናቸው።


እና​ንት የጽ​ዮን ቈነ​ጃ​ጅት፥ እናቱ በሠ​ርጉ ቀን በልቡ ደስታ ቀን ያቀ​ዳ​ጀ​ች​ውን አክ​ሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎ​ሞ​ንን ታዩ ዘንድ ውጡ።


እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ጡቶ​ችሽ እን​ዴት ያማሩ ናቸው? ጡቶ​ችሽ ከወ​ይን ይልቅ እጅግ ያማሩ ናቸው። የሽ​ቱ​ሽም መዓ​ዛው ከሽቱ ሁሉ ይልቅ እጅግ ያማረ ነው።


እኅቴ ሙሽ​ሪት የተ​ቈ​ለ​ፈች ገነት፥ የተ​ዘ​ጋች ገነት፥ የታ​ተ​መ​ችም ጕድ​ጓድ ናት።


በዚያ ጡቶ​ችን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፥ ሰው​ነ​ቴም አላ​ወ​ቀ​ችም፥ እንደ አሚ​ና​ዳብ ሰረ​ገላ አደ​ረ​ገኝ አለች። ብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አይ ዘንድ ... ወረ​ድሁ” ይላል። ወይኑ አብቦ ሮማ​ኑም አፍ​ርቶ እንደ ሆነ ይመ​ለ​ከት ዘንድ ወደ ገውዝ ገነት ወረደ።


ዐይ​ኖ​ች​ሽን ከፊቴ መልሺ፤ እነ​ርሱ አስ​ፈ​ር​ተ​ው​ኛ​ልና፤ ጠጕ​ርሽ ከገ​ለ​ዓድ እንደ ታየ እንደ ፍየል መንጋ ነው።


ጕሮ​ሮ​ሽም ለልጅ ወን​ድሜ እየ​ጣ​ፈጠ እን​ደ​ሚ​ገባ፥ ለከ​ን​ፈ​ሮ​ችና ለም​ላሴ እን​ደ​ሚ​ስ​ማማ እንደ ማለ​ፊያ የወ​ይን ጠጅ ነው።


ፈጣ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ታዳ​ጊሽ ነው፤ እር​ሱም በም​ድር ሁሉ እን​ደ​ዚሁ ይጠ​ራል።


ጐል​ማ​ሳም ከድ​ን​ግ​ሊቱ ጋር እን​ደ​ሚ​ኖር፥ እን​ዲሁ ልጆ​ችሽ ከአ​ንቺ ጋር ይኖ​ራሉ፤ ሙሽ​ራም በሙ​ሽ​ራ​ዪቱ ደስ እን​ደ​ሚ​ለው፥ እን​ዲሁ አም​ላ​ክሽ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ዋል።


በጌ​ጥም አስ​ጌ​ጥ​ሁሽ፤ በእ​ጅ​ሽም ላይ አን​ባር፥ በአ​ን​ገ​ት​ሽም ላይ ድሪ አደ​ረ​ግ​ሁ​ልሽ።


በአ​ንቺ ዘንድ በአ​ለ​ፍ​ሁና በአ​የ​ሁሽ ጊዜ፥ እነሆ ጊዜሽ እንደ ደረሰ፥ በአ​ን​ቺም የሚ​ያ​ድሩ ሰዎች ጊዜ እንደ ደረሰ አየሁ። እጆ​ችን በላ​ይሽ ዘረ​ጋሁ፤ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ሽ​ንም ከደ​ንሁ፤ ማል​ሁ​ል​ሽም፤ ከአ​ን​ቺም ጋራ ቃል ኪዳን ገባሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ቺም ለእኔ ሆንሽ።


አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፣ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።


በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና፤” አለ።


ሙሽራ ያለ​ችው ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚ​ሰ​ማው የሙ​ሽ​ራው ሚዜ ግን በሙ​ሽ​ራው ቃል እጅግ ደስ ይለ​ዋል፤ የእኔ ደስታ አሁን ተፈ​ጸ​መች።


እንደ ሌሎች ሐዋ​ር​ያት ሁሉና፥ እንደ ጌታ​ችን ወን​ድ​ሞች እንደ ኬፋም ከሴ​ቶች እኅ​ታ​ች​ንን ይዘን ልን​ዞር አይ​ገ​ባ​ን​ምን?


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገባ ቅን​ዐት እቀ​ና​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁና፤ ወደ እርሱ አቀ​ር​ባ​ችሁ ዘንድ ለአ​ንዱ ንጹሕ ድን​ግል ሙሽራ ለክ​ር​ስ​ቶስ አጭ​ቻ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።


跟着我们:

广告


广告