Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 4:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ከሊ​ባ​ኖስ ነዪ፤ ከሊ​ባ​ኖስ ነዪ፤ ከሃ​ይ​ማ​ኖት ራስ ከሳ​ኔ​ርና ከኤ​ር​ሞን ራስ፥ ከአ​ን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ፥ ከነ​ብ​ሮ​ችም ተራራ ተመ​ል​ከቺ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሙሽራዬ ሆይ፤ ከሊባኖስ ዐብረሽኝ ነዪ፤ አዎን ከሊባኖስ ዐብረሽኝ ነዪ፤ ከአንበሶች ዋሻ፣ ከነብሮች ተራራ፣ ከአርሞን ራስ፣ ከሳኔር ጫፍ፣ ከአማና ዐናት ውረጂ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥ ከአማና ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ፥ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ወደ እኔ ነይ፤ ከሊባኖስ ወደ እኔ ነይ፤ ከአማና ተራራ ጫፍ ውረጂ፤ የአንበሳና የነብር መኖሪያ ከሆኑት ከሠኒርና ከሔርሞን ተራራዎች ወርደሽ ነይ

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥ ከአማና ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ፥ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 4:8
19 交叉引用  

ስለ ዛፍም ከሊ​ባ​ኖስ ዝግባ ጀምሮ በቅ​ጥር ግንብ ላይ እስ​ከ​ሚ​በ​ቅ​ለው እስከ አሽ​ክት ድረስ ይና​ገር ነበር፤ ደግ​ሞም ስለ አው​ሬ​ዎ​ችና ስለ ወፎች ስለ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችና ስለ ዓሣ​ዎች ይና​ገር ነበር።


የደ​ማ​ስቆ ወን​ዞች ባብ​ናና ፋርፋ ከእ​ስ​ራ​ኤል ውኆች ሁሉ አይ​ሻ​ሉ​ምን? ሄጄስ በእ​ነ​ርሱ ውስጥ መጠ​መ​ቅና መን​ጻት አይ​ቻ​ለ​ኝም ኖሮ​አ​ልን?” ብሎ በቍጣ ተመ​ልሶ ሄደ።


የም​ና​ሴም የነ​ገድ እኩ​ሌታ ልጆች፤ ከባ​ሳን ጀምሮ እስከ በኣ​ል​አ​ር​ሞ​ንና እስከ ሳኔር እስከ አር​ሞ​ን​ኤም ተራራ እስከ ሊባ​ኖስ ድረስ ተቀ​መጡ፤ እነ​ር​ሱም በዙ።


ልብ አድ​ርጉ፥ እኔም አም​ላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላ​ለሁ፥ በም​ድ​ርም ላይ ከፍ ከፍ እላ​ለሁ።


አው​ቅም ዘንድ ተቀ​በ​ል​ኸኝ፥ ይህ ግን በፊቴ ድካም ነው።


በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፥ ቃሌም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ እር​ሱም አደ​መ​ጠኝ።


ደነ​ገ​ጥሁ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁ​ምም።


ጥበ​ብን በልብ ለተ​ማሩ፥ ቀኝ​ህን እን​ዲህ ግለጥ።


ስንፍናን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በሕይወትም ትኖሩ ዘንድ ዕውቀትን ፈልጉ፥ በመረዳትም ዕውቀትን አቅኑ።”


በለሱ ጐመራ፥ ወይ​ኖ​ችም አበቡ፥ መዓ​ዛ​ቸ​ው​ንም ሰጡ፤ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፤ መል​ካ​ምዋ ርግቤ ሆይ፥ ነዪ። በዐ​ለት ንቃ​ቃ​ትና በገ​ደል መሸ​ሸ​ጊያ ወዳ​ለው ጥላ ነዪ።


እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከር​ቤ​ዬን ከሽ​ቱዬ ጋር ለቀ​ምሁ፥ እን​ጀ​ራ​ዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወ​ይን ጠጄን ከወ​ተቴ ጋር ጠጣሁ። ባል​ን​ጀ​ሮች በሉ፥ ጠገ​ቡም፤ የወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ጠጡ፥ ሰከ​ሩም፥ ልባ​ቸው የጠፋ ነውና።


እኔ የልጅ ወን​ድሜ ነኝ፥ የእ​ር​ሱም መመ​ለ​ሻው ወደ እኔ ነው።


ጐል​ማ​ሳም ከድ​ን​ግ​ሊቱ ጋር እን​ደ​ሚ​ኖር፥ እን​ዲሁ ልጆ​ችሽ ከአ​ንቺ ጋር ይኖ​ራሉ፤ ሙሽ​ራም በሙ​ሽ​ራ​ዪቱ ደስ እን​ደ​ሚ​ለው፥ እን​ዲሁ አም​ላ​ክሽ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ዋል።


ሳን​ቃ​ዎ​ች​ሽን ሁሉ ከሳ​ኔር ጥድ ሠር​ተ​ዋል፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ሽ​ንም ይሠ​ሩ​ልሽ ዘንድ ከሊ​ባ​ኖስ ዝግ​ባን ወስ​ደ​ዋል።


እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ ካለ ይከ​ተ​ለኝ፤ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ እኔ ባለ​ሁ​በት በዚያ ይኖ​ራ​ልና፤ እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ኝ​ንም አብ ያከ​ብ​ረ​ዋል።


እኔ እን​ድ​ሻ​ገ​ርና፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ያለ​ች​ውን መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር፥ ያንም መል​ካ​ሙን ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር አንጢ ሊባ​ኖ​ስ​ንም እን​ዳይ ፍቀ​ድ​ልኝ።


ፊኒ​ቃ​ው​ያን ኤር​ሞ​ንን “ሳኒ​ዮር” ብለው ይጠ​ሩ​ታል፤ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ሳኔር ብለው ይጠ​ሩ​ታል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የመ​ቱ​አ​ቸው፥ ከአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አር​ሞ​ን​ዔም ተራራ ድረስ በም​ሥ​ራቅ በኩል ያለ​ውን ዓረባ ሁሉ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ በፀ​ሐይ መውጫ ያለ​ውን ሀገ​ራ​ቸ​ውን የወ​ረ​ሱ​አ​ቸው የም​ድር ነገ​ሥት እነ​ዚህ ናቸው፤


跟着我们:

广告


广告