Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ጥር​ሶ​ችሽ ከመ​ታ​ጠ​ቢያ ወጥ​ተው እንደ ተሸ​ለቱ ሁሉም መንታ መንታ እንደ ወለዱ ከእ​ነ​ር​ሱም መካን እን​ደ​ሌ​ለ​ባ​ቸው መን​ጎች ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ጥርሶችሽ ወዲያው ተሸልተው፣ ከመታጠቢያ እንደ ወጡ የበግ መንጋ ናቸው፤ ሁሉም መንታ መንታ የወለዱ፣ ከመካከላቸውም መካን የሌለባቸው ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ተሸለቱ ሁሉም መንታ እንደ ወለዱ ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ጥርሶችሽ፥ በመካከላቸው ምንም መኻን ሳይኖርባቸው መንታ መንታ እንደሚወልዱ፥ ተሸልተው በውሃ እንደ ታጠቡ፥ ነጫጭ የበጎች መንጋ ደስ ያሰኛሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ተሸለቱ ሁሉም መንታ እንደ ወለዱ ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 4:2
10 交叉引用  

በም​ድ​ር​ህም መካን፥ ወይም የማ​ይ​ወ​ልድ አይ​ኖ​ርም፤ የዘ​መ​ን​ህ​ንም ቍጥር እሞ​ላ​ለሁ።


ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤ ከዝ​ም​ታሽ በቀር ዐይ​ኖ​ችሽ እንደ ርግ​ቦች ናቸው፤ ጠጕ​ርሽ በገ​ለ​ዓድ ተራራ እን​ደ​ሚ​ታይ እንደ ፍየል መንጋ ነው።


ከን​ፈ​ሮ​ችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ናቸው፥ ቃል​ሽም ያማረ ነው፤ ከዝ​ም​ታሽ በቀር ጕን​ጮ​ችሽ እንደ ተከ​ፈለ ሮማን ናቸው።


ጥር​ሶ​ችሽ ታጥ​በው እንደ ወጡ ሁሉም መንታ እንደ ወለዱ ከእ​ነ​ር​ሱም መካን እን​ደ​ሌ​ለ​ባ​ቸው መን​ጎች ናቸው። ከን​ፈ​ሮ​ችሽ እንደ ቀይ ሐር ናቸው፥ ቃልሽ ያማረ ነው።


ቃልህ ተገ​ኝ​ቶ​አል፤ እኔም በል​ች​ዋ​ለሁ፤ አቤቱ! የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ ሆይ! ቃል​ህን የከዱ ሰዎ​ችን አጥ​ፋ​ቸው፤ ስምህ በእኔ ላይ ተጠ​ር​ት​ዋ​ልና፥ ቃልህ ሐሤ​ትና የልብ ደስታ ሆነኝ።


በእ​ኔም ብት​ኖሩ ቃሌም በእ​ና​ንተ ቢኖር የም​ት​ሹ​ትን ሁሉ ትለ​ም​ና​ላ​ችሁ፤ ይደ​ረ​ግ​ላ​ች​ሁ​ማል።


ስለዚህም የመልእክትን ቃል እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በምታምኑ ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን።


跟着我们:

广告


广告