Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 4:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የሰ​ሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥ የደ​ቡ​ብም ነፋስ ና፤ በገ​ነቴ ላይ ንፈስ፥ ሽቱ​ዬም ይፍ​ሰስ፤ ልጅ ወን​ድሜ ወደ ገነቱ ይው​ረድ፥ መል​ካ​ሙ​ንም ፍሬ ይብላ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የሰሜን ነፋስ ሆይ፤ ንቃ፤ የደቡብም ነፋስ ሆይ፤ ና! መዐዛው ያውድ ዘንድ፣ በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ፤ ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባ፤ ምርጥ ፍሬዎቹንም ይብላ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የሰሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥ የደቡብም ነፋስ ና፥ በገነቴ ላይ ንፈስ፥ ሽቱውም ይፍሰስ፥ ውዴ ወደ ገነቱ ይግባ ምርጡንም ፍሬ ይብላ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የሰሜን ነፋስ ሆይ! ንቃ! አንተም የደቡብ ነፋስ ሆይ! ወደዚህ ና! በአትክልት ቦታዬም ላይ ንፈስ፤ ዐየሩም በመልካም ሽታ የተሞላ ይሁን፤ ውዴም ወደ አትክልት ቦታው ይምጣ፤ ምርጥ የሆኑትንም ፍሬዎች ይመገብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የሰሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥ የደቡብም ነፋስ ና፥ በገነቴ ላይ ንፈስ፥ ሽቱውም ይፍሰስ፥ ውዴ ወደ ገነቱ ይግባ መልካሙንም ፍሬ ይብላ።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 4:16
30 交叉引用  

ወደ ቀኝ ይመ​ለ​ሳል፥ ወደ ሰሜ​ንም ይዞ​ራል፤ ነፋስ ዙሪ​ያ​ዉን ዙሮ ይሄ​ዳል፥ ነፋ​ስም በዙ​ረቱ ይመ​ለ​ሳል።


የወ​ይ​ንና የአ​ት​ክ​ልት ቦታን አደ​ረ​ግሁ፥ ወይ​ንና ልዩ ልዩ ፍሬ ያለ​ባ​ቸ​ው​ንም ዛፎች ተከ​ል​ሁ​ባ​ቸው።


ውዴ ለእኔ በጡ​ቶች መካ​ከል እን​ደ​ሚ​ያ​ርፍ እንደ ተቋ​ጠረ ከርቤ ነው።


ከወደ ኋላ​ህም ሳቡህ፥ በሽ​ቱህ መዓ​ዛም እን​ሮ​ጣ​ለን፤ ንጉሡ ወደ እል​ፍኙ አገ​ባኝ፤ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ኛል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ ከወ​ይን ጠጅ ይልቅ ጡቶ​ች​ሽን እን​ወ​ዳ​ለን፤ አን​ቺ​ንም መው​ደድ የተ​ገባ ነው።


በዱር እን​ዳለ እን​ኮይ፥ እን​ዲሁ ውዴ በወ​ን​ድ​ሞች መካ​ከል ነው። ከጥ​ላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀ​መ​ጥሁ፥ ፍሬ​ውም ለጕ​ሮ​ሮዬ ጣፋጭ ነው።


እነሆ፥ የልጅ ወን​ድሜ ቃል በተ​ራ​ሮች ላይ ሲዘ​ልል፥ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ሲወ​ረ​ወር ይመ​ጣል።


እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከር​ቤ​ዬን ከሽ​ቱዬ ጋር ለቀ​ምሁ፥ እን​ጀ​ራ​ዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወ​ይን ጠጄን ከወ​ተቴ ጋር ጠጣሁ። ባል​ን​ጀ​ሮች በሉ፥ ጠገ​ቡም፤ የወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ጠጡ፥ ሰከ​ሩም፥ ልባ​ቸው የጠፋ ነውና።


ልጅ ወን​ድሜ በገ​ነቱ መን​ጋ​ውን ይጠ​ብቅ ዘንድ፥ አበ​ባ​ው​ንም ይሰ​በ​ስብ ዘንድ ወደ ሽቱ መደብ ወደ ገነቱ ወረደ።


ለእኔ ያለኝ የወ​ይን ቦታ በፊቴ ነው፤ አንዱ ሺህ ለሰ​ሎ​ሞን፥ ሁለቱ መቶ ፍሬ​ውን ለሚ​ጠ​ብቁ ነው።


ሰማ​ይን ብት​ከ​ፍት ከአ​ንተ የተ​ነሣ ተራ​ሮች ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ይቀ​ል​ጣ​ሉም።


እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለነ​ፋስ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለነ​ፋ​ስም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ! ከአ​ራቱ ነፋ​ሳት ዘንድ ና፤ እነ​ዚህ ሙታን በሕ​ይ​ወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በል​ባ​ቸው በል” አለኝ።


ኢየሱስም ይህን አውቆ እንዲህ አላቸው “መልካም ሥራ ሠርታልኛለችና ሴቲቱንስ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ?


እርስዋ ይህን ሽቱ በሰውነቴ ላይ አፍስሳ ለመቃብሬ አደረገች።


ነፋስ ወደ ወደ​ደው ይነ​ፍ​ሳ​ልና፤ ድም​ፁ​ንም ትሰ​ማ​ለህ፤ ነገር ግን ከየት እን​ደ​ሚ​መጣ ወዴ​ትም እን​ደ​ሚ​ሄድ አታ​ው​ቅም፤ ከመ​ን​ፈስ የሚ​ወ​ለድ ሁሉ እን​ዲሁ ነው።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ተነ​ሥና አል​ጋ​ህን ተሸ​ክ​መህ ሂድ” አለው።


ሲጸ​ል​ዩም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩ​በት ቦታ ተና​ወጠ፤ በሁ​ሉም ላይ መን​ፈስ ቅዱስ መላ​ባ​ቸ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በግ​ልጥ አስ​ተ​ማሩ።


በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግል ዘንድ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወን​ጌ​ልም እገዛ ዘንድ፥ በእኔ ትም​ህ​ርት አሕ​ዛብ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የተ​ወ​ደ​ደና የተ​መ​ረጠ መሥ​ዋ​ዕት ይሆኑ ዘንድ።


እን​ግ​ዲህ ይህን ፍሬ ጨር​ሼና አትሜ በእ​ና​ንተ በኩል ወደ አስ​ባ​ንያ እሄ​ዳ​ለሁ።


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


跟着我们:

广告


广告