Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እነሆ፥ የሰ​ሎ​ሞን አልጋ ናት፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ኀያ​ላን ስድሳ ኀያ​ላን በዙ​ሪ​ያዋ ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እነሆ፤ የሰሎሞን ሠረገላ በታዋቂዎቹ የእስራኤል መኳንንት፣ ስድሳ ጦረኞች ታጅባለች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እነሆ፥ የሰሎሞን አልጋ ናት፥ ከእስራኤል ኃያላን መካከል ስድሳ ኃያላን በዙሪያው ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እነሆ፥ የሰሎሞን ሠረገላ እየመጣች ነው፤ ከእስራኤል ኀያላን መካከል የተመረጡ ሥልሳ የክብር ዘበኞች አጅበዋታል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እነሆ፥ የሰሎሞን አልጋ ናት፥ ከእስራኤል ኃያላን ስድሳ ኃያላን በዙሪያው ናቸው።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 3:7
12 交叉引用  

ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም በፋ​ን​ታው የናስ ጋሾ​ችን ሠራ፤ በፊ​ቱም ለሚ​ሮ​ጡና የን​ጉ​ሥን ቤት ደጅ ለሚ​ጠ​ብቁ የዘ​በ​ኞች አለ​ቆች ሰጣ​ቸው።


ሰሎ​ሞ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማን​ንም ገባር አላ​ደ​ረ​ገም፤ እነ​ርሱ ግን ተዋ​ጊ​ዎች፥ ሎሌ​ዎ​ችም፥ መሳ​ፍ​ን​ትም፥ አለ​ቆ​ችም፥ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና የፈ​ረ​ሶች ባል​ደ​ራ​ሶች ነበሩ።


ኤል​ሳ​ዕም፥ “አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዐይ​ኖ​ቹን፥ እባ​ክህ፥ ግለጥ” ብሎ ጸለየ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የብ​ላ​ቴ​ና​ውን ዐይ​ኖች ገለጠ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ሳት ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎች በኤ​ል​ሳዕ ዙሪያ ተራ​ራ​ውን ሞል​ተ​ውት አየ።


ከቅ​ጥ​ሩም በስ​ተ​ኋላ በኩል ባለው በታ​ች​ኛው ክፍል በሰ​ዋራ ስፍራ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንና ጦራ​ቸ​ውን፥ ቀስ​ታ​ቸ​ው​ንም አስ​ይዤ ሕዝ​ቡን በየ​ወ​ገ​ና​ቸው አቆ​ም​ኋ​ቸው፤


ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ውብ ነህ፥ መልከ መል​ካ​ምም ነህ፤ አል​ጋ​ች​ንም ለም​ለም ነው።


መዓ​ዛዋ እንደ ከር​ቤና እንደ ዕጣን የሆ​ነው፥ ከልዩ የሽቱ ቅመም ሁሉ የሆ​ነው፥ ይህች ከም​ድረ በዳ እንደ ጢስ ዐምድ የወ​ጣ​ችው ማን ናት?


ሁሉም ሰይፍ የያ​ዙና ሰልፍ የተ​ማሩ ናቸው፤ በሌ​ሊት ከሚ​ወ​ድ​ቀው ፍር​ሀት የተ​ነሣ ሰው ሁሉ ሰይፉ በወ​ገቡ አለ።


ንጉሡ ሰሎ​ሞን መሸ​ከ​ሚ​ያን ከሊ​ባ​ኖስ እን​ጨት ለራሱ አሠራ።


መላ​እ​ክት ሁሉ መና​ፍ​ስት አይ​ደ​ሉ​ምን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይወ​ርሱ ዘንድ ስለ አላ​ቸው ሰዎ​ችስ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ይላኩ የለ​ምን?


በሳ​ኦ​ልም ዘመን ሁሉ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጽኑ ውጊያ ነበረ፤ ሳኦ​ልም ጽኑ ወይም ኀያል ሰው ባየ ጊዜ ወደ እርሱ ይሰ​በ​ስብ ነበር።


ዳዊ​ትም አን​ኩ​ስን፥ “አሁን አገ​ል​ጋ​ይህ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ንገ​ረው” አለው። አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “እን​ግ​ዲህ በዘ​መኑ ሁሉ ራሴን ጠባቂ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” አለው።


ሎሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁ​ንና ገረ​ዶ​ቻ​ች​ሁን፥ ከከ​ብ​ቶ​ቻ​ች​ሁና ከአ​ህ​ዮ​ቻ​ች​ሁም መል​ካም መል​ካ​ሙን ወስዶ ያሠ​ራ​ቸ​ዋል።


跟着我们:

广告


广告